በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ የካቲት 4, 2014) 1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,569
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 14,588
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 6,557
በቁጥር (ከጥር 28, 2014 እስከ የካቲት 4, 2014) 2 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 17
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 134
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 12
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ሃይሎች እና በአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች እንዲሁም ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም በቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በትህነግ ሃይሎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ከቡድኑ ጋርም ውጊያ አድርጓል። በበርሃሌ፣ ኮነባ፣ መጋሌ፣ እና ኢረብቲ አከባቢዎች ውጊያዎች መከሰታቸው ተዘግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የአፋር ክልል መንግስት ትህነግ በቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በኩል ውጊያ በድጋሚ የጀመረው በኢትዮጵያ-ጅቡቲ መስመር ወሳኝ የሆነውን የሰርዶ ፍተሻ ኬላ ለመቆጣጠር ነው ብሏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። የሰርዶ ፍተሻ ኬላ የኢትዮጵያ ብቸኛ የባህር መዳረሻ የሆነውን የጅቡቲ ወደብ ትራፊክን ይቆጣጠራል።
ባለፈው ሳምንት የአክሌድ መረጃ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ የተሳተፈባቸው ውጊያዎችን እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን በኦሮሚያ ክልል መዝግቧል። ጥር 28 ላይ የኦነግ-ሸኔ አባላት በጉጂ ዞን ዋዴራ ወረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኪናን አድፍጠው ማጥቃታቸው ተዘግቧል። ከሁለት ቀናት በኋላ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በየመከራ ዳገት (ኤርሻን አኖ) በተባለ አካባቢ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን አንዳንድ ምስክሮች ግን ኦነግ-ሸኔ ነው ብለው የጠረጠሩት ቡድን ሶስት የጭነት መኪኖች ላይ ጥቃት በማድረስ ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ሲገድል አራት ተጨማሪ ሰዎችን አቁስሏል። ታጣቂ ቡድኑ መኪኖቹ እያጓጓዙት የነበሩትን ምርቶችም ዘርፈዋል። የካቲት 2 በተፈጠረ ሌላ ኩነት የኦነግ-ሸኔ አባላት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋረ ጃርሶ ወረዳ ኮቲቻ አካባቢ እያለፈ የነበረ የጭነት መኪና አጥቅተው አሽከርካሪውን ገድለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። ይህንን ጥቃት ተከትሎ ከአካባቢው የፖሊስ ሃይሎች ጋር ውጊያ ተካሂዷል። ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ አዘውትረው የሚጓዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት በዚህ አካባቢ ለመጓዝ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም አሽከርካሪዎቹ በአማራ ክልል ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ሊደርስብን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል። እንደ አሽከርካሪዎቹ ገለጻ በአማራ ክልል በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እየታፈኑ እና ጥቃት እየደረሰባቸው ነው (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 7, 2014)።
ባለፈው ሳምንት መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የምትገኘውን ጊዳሚ ወረዳን በቁጥጥሩ ስር መዋሉን በይፋ አስታውቋል። ኦነግ-ሸኔ አካባቢውን ለወራት ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች አካባቢውን ጥር 9 ላይ መልሰው ተቆጣጥረዋል። የመንግስት ሃይሎች ቦታውን ከያዙ በኋላ 87 ሰዎች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር መገኘቱን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች አሁንም እንደጠፉ የመንግስት ባለስልጣናት ጠቁመዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ጥር 30, 2014)። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች በ1970ዎቹ በድርቅ ከተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሰፈሩ አማራዎች እንደሆኑ ይታመናል። በተጨማሪም ኦነግ-ሸኔ እነዚህን ቦታዎች በተቆጣጠረበት ወቅት 105 የመንግስት ሰራተኞች ከጊዳሚ እንዲሁም 63 ከአጎራባች የኮንዳላ እና ቤጊ ወረዳዎች ማፈኑ ተዘግቧል። የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ ይህንን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ የመንግስት ሃይሎች “የመከበብ አደጋ ላይ በመሆናቸው” የመንግስትየመገናኛ ብዙሃን ዘገባውን “ፈጥረዋል” ሲሉ ከሰዋል (ትዊተር ኦዳ ታርቢ፣ የካቲት 1, 2014)።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን በዱዌ ሃራ በሚገኘው ደዋ ጨፋ እና ስንቅሌ የሚገኙ የኦነግ-ሸኔ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ ጥቃት በማድረስ 100 ታጣቂዎችን መግደላቸው ተዘግቧል። የእነዚህን ካምፖች መውደም ተከትሎ 600 የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች መታሰራቸው ተዘግቧል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ጥር 30, 2014)። ዞኑ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባሳለፍነው አመት ከፍተኛ ብጥብጥ ሲካሄድበት ቆይቷል። የመንግስት ሃይሎች በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የወሰዱት እርምጃ “በሺዎች” የሚቆጠሩ ሰዎችን ለእስራት እና ብዙ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳርጓል (አዲስ ስታንዳርድ፣ የካቲት 8, 2014)።
በተጨማሪም ጥር 30 ላይ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በማረሚያ ቤት፣ ፖሊስ ጣቢያ፣ እና በአካባቢው የታጣቂዎች ጽ/ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጦር መሳሪያ ዘርፈው እስረኞችን ከማረሚያ ቤት አስመልጠዋል። አስራ ስድስት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች 20 ደግሞ ተይዘዋል። ሶስት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አባላትም ቆስለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 1, 2014)። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ይህ ታጣቂ ቡድን እራሱን “ፋኖ” እያለ ቢገልጽም የመዋቅሩ አካል ነን ማለታቸውን ውድቅ አድርጓል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ የካቲት 1, 2014)። የፋኖ ታጣቂዎች በባህሪያቸው መደበኛ ያልሆኑ እና ለመለየት የሚያስቸግሩ ናቸው (የፋኖ ወጣት ታጣቂን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቡድኖች መግለጫን ይመልከቱ)። በአማራ ክልል መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂዎች – የፋኖ ቡድኖችን ጨምሮ – የታጠቁትና የሰለጠኑት ትህነግ/ህወሓትን ለመዋጋት ነበር። የእነዚህ ታጣቂዎች ኢ-መደበኛ ባህሪ መንግስትን ያሳሰበው ሲሆን እንዲሁም በጥር ወር አጋማሽ ላይ ባለስልጣናት ቡድኑን ወደ ነባር የጸጥታ መዋቅር ለማዋሃድ ሲወያዩ ነበር (ፋና ቴሌቪዥን፣ ጥር 20, 2014)።
በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በተለያዩ የክልሉ ዞኖች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ባለፈው ሳምንት በክልሉ ሶስት ጥቃቶችን አድርሰው አራት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለዋል። የካቲት 2 ላይ ቡድኑ በአኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ ኡኩቡ አካባቢ ባለ የስደተኞች ካምፕ ባደረሰው ጥቃት ሁለት ሴቶች ሲቆስሉ ሶስት ህጻናት ታፍነው ተወስደዋል። በማግስቱ በአኝዋክ ዞን ጎግ ወረዳ አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ተኩሰው ገድለዋል። የካቲት 4 ላይ በጎግ ወረዳ ጃንጆር ቀበሌ የቡድኑ አባላት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን አጥቅተው ሶስት ሰዎች ገድለዋል። በተጨማሪም ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን የሚጓዝ የጭነት መኪና አጥቅተው ሹፌሩንና ረዳቱን ገድለዋል። የፌደራል ፖሊስ እና የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ጥቃቱን ለማጣራት እና የተወሰዱትን ህጻናት ለማግኘት በቅንጅት እየሰሩ ነው (የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ የካቲት 4, 2014)። ከደቡብ ሱዳን የሆኑ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚያደርሷቸው ጥቃቶች ባለፉት ሶስት ሳምንታት ጨምረዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቃቶች የተፈጸሙት ባለፈው ሳምንት ነው።
ሳምንታዊ ትኩረት፡ በኢትዮጵያ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በመንግስት ላይ የፈጠሩት ጫና
የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዛት ለመጨመር ጥረት ቢያደርግም እየተከሰቱ ያሉ በርካታ ቀውሶች የመንግስትን ሃብት እያጣበቡ ነው። በአፋር እና ምዕራብ ኦሮሚያ እየተካሄደ ላለው ግጭት መንግስት ምላሽ መስጠት አለመቻሉ ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፍተኛ ትችት ፈጥሯል።
በአፋር ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ውጊያ የመኖሪያ ከተሞች በሆኑት በመጋላ፣ ኮነባ፣ እና በርሃሌ ባሉ ከተሞች በመድረስ የዜጎችን ህይወትና ደህንነት እያሰጋ ነው ( (የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ የካቲት 3, 2014)። የአፋር ክልል ባለስልጣናት ባለፈው ወር ያገረሸው ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ እስከ 430,000 የሚደርሱ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በመኖሪያ ህንጻዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት እንደሆነ ይገመታል (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 2, 2014)። ከትህነግ/ህወሓት ጋር በሚደረገው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎችን እና ታጣቂዎችን እየደገፉ ቢሆንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምድር ጦር ግን በጣም አነስተኛ ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነ ባለስልጣናቱ አሳውቀዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 30, 2014)።
ጸጥታ ሃይሎቹ በእነዚህ ተመሳሳይ ተግዳሮቶች የተዋጡበት የምዕራብ ጉጂ አስተዳደርም በተመሳሳይ “የፌዴራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ለቀውሱ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል” (አዲስ ስታንዳርድ፣ የካቲት 3, 2014)።
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት የፌደራል ሃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ – በክልል የጸጥታ ጉዳዮች ላይ በክልሉ ባለስልጣናት ሲጋበዙ ወይም የክልሉ የጸጥታ ሃይሎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ መቆጣጠር በማይችሉበት ጊዜ ብቻ ጣልቃ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል (የኢፌዴሪ ህገመንግስት 1987፣ አንቀጽ 51 (14))። በሌሎች ጉዳዮች ሁሉ የጸጥታ ጉዳዮች የአካባቢ ወይም የክልል መንግስታት ኃላፊነት ናቸው።
ባለፈው ሳምንት በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ ያወጡ ሲሆን መንግስት ዳግም ለተቀሰቀሰው ጦርነት እና መፈናቀል የሰጠውን ደካማ ምላሽ ተችተዋል። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የተፈፀመውን ግድያ አስመልክቶ መግለጫ አውጥተዋል። አብን መንግስት በክልሉ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለመከላከል እርምጃ አልወሰደም ሲል ከሶ መንግስት ድርጊቱን በፈጸሙት ላይ እርምጃ እንዲወስድና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል (የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የካቲት 2, 2014)። በተመሳሳይ ኢዜማ በኦነግ-ሸኔ ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። ኢዜማ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ማንነትን መሰረት ካደረገ ጥቃት መከላከል አልቻለም ሲል የከሰሰ ሲሆን የክልሉ መንግስት ቸልተኝነት ለኦነግ-ሸኔ ተቋማዊ ድጋፍ የመስጠቱ ምልክት ነው ብሏል (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ፣ የካቲት 1, 2014)።
ብዙን ጊዜ በተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በገዢው የብልጽግና ፓርቲ መካከል ያለው ውጥረት አለመረጋጋት ባለበት ወቅት ይባባሳል። ሚያዝያ 2013 ላይ በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚደርሱ ጥቃቶችን ተከትሎ የብልፅግና ፓርቲን የሚቃወሙ እና የመንግስትን እርምጃ አለመውሰድ የሚነቅፉ ሰልፎች በአማራ ክልል ተካሂደዋል (ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከመጋቢት 23, 2013 እስከ ሚያዚያ 22, 2013 ይመልከቱ)። ከትህነግ/ህወሃት ጋር በነበረው ውጊያ ወቅት አብን መንግስትን ብዙ ጊዜ ስህተቶችን በመፈጸም ከሷል። ባለፈው ሳምንትም አብን የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች እንደገና ተደራጅተው አማራ ክልልን በድጋሚ ሊያጠቁ ይችላሉ የሚል ፍራቻውን ገልጿል። በመሆኑም አብን በእነዚህ አካባቢዎች የሚደርሰውን የትህነግ/ህወሃትን ጥቃት ለመመከት የፌደራል መንግስት ለአፋር ክልል እንዲሁም ለራያ እና ጸለምት ህዝቦች አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል (የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፣ የካቲት 2, 2014)።
እነዚህ ትችቶች ቢኖሩም መንግሥት የሀገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል በርካታ ጥረቶችን አድርጓል። የኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት ጥር 6 ላይ ያለውን ሁከትና ብጥብጥ በተመለከተ ለመምከር የተሰበሰበ ሲሆን ጥቅምት 23 ላይ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል (ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥቅምት 20, 2014 እስከ ጥቅምት 26, 2014 ይመልከቱ)። እንደ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤው ታገሰ ጫፎ የመንግስት ሃይሎች በአማራ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመንግስት ሃይሎች “የእርምት እርምጃዎች” ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል (የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የካቲት 7, 2014)። በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን ያሉ አካባቢዎች ሰፊ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው (ኢቢሲ፣ የካቲት 1, 2014)። የፌደራል ሃይሎች ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና ጥይቶች ዝውውርን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን ወደ ግጭት አካባቢ የሚካሄዱ ዝውውሮችን በየጊዜው እየያዘ ይገኛል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የካቲት 3, 2014)።
በአገር ውስጥ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከኬንያው ብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ኮሚሽን ከፍተኛ መኮንን ጋር በጋራ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ሁለቱ ባለስልጣናት በኦነግ-ሸኔ እና አልሸባብ ታጣቂዎች ላይ “የጋራ ዘመቻ” ለመጀመር ተስማምተዋል (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ጥር 7, 2014)።
የክልሉ መንግስት ባለስልጣናትም በመላ ሀገሪቱ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሳምንቱ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተለያዩ የአገሪቱን ክልሎች ጎብኝተው የሰላምና ፀጥታ ማስተባበርና የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋምን ያካተተ አጀንዳዎችን ያጠናከሩ ሲሆን ይህም የክልል ባለስልጣናት የተሻለ የውስጥ ግንኙነት ለመፍጠር እየሞከሩ እንደሆነ አመላካች ነው (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የካቲት 4, 2014)። ባለፈው ሳምንት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ድንበር ዘለል ጥቃቶችን ለመግታት ደቡብ ሱዳንን ጎብኝተዋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ጥር 25, 2014)። በአማራ ክልል የክልሉ ባለስልጣናት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ሃላፊነት የተሰጠው ጽ/ቤት አቋቁመዋል (ኢትዮጵያ ኢንዳይደር፣ ጥር 26, 2014)።