በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሚያዚያ 7, 2014-ሚያዚያ 13, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,123
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,068
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,597
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሚያዚያ 7-13, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 2
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 10
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 10
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኢትዮጵያ ሁለት አበይት ሐይማኖታዊ በዓላት ማለትም ፋሲካ እና ኢድ አል-ፈጥር በተከበሩበት ባለፈው ሳምንት ቀደም ካለው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የፖለቲካ ግጭት ቀንሷል። በአድዋ እና ባለፈው አመት በተከበረው የኢድ በዓል ላይ መጠነኛ ግጭት ተነስቶ የነበረ ቢሆንም (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 18–24, 2015 እና ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሚያዚያ 15-28, 2014 ይመልከቱ) በትንሳኤ እና በዘንድሮ የኢድ በዓላት ምንም ግጭት ሳይዘገብ ተከብረው ውለዋል።
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሚያዚያ 9 ቀን የአማራ ብሔር ታጣቂዎች በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጅልዬ ጥሙጋ ወረዳ በባቴ አርዳጋ ቀበሌ በኦሮሞ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። በጥቃቱ ቢያንስ 10 ሰዎች ሲሞቱ ቤቶች ተቃጥለዋል የቀንድ ከብቶችም ተዘርፈዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሚያዚያ 10 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ከ50 የሚበልጡ ታጣቂዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኒ ዓለም ቤተክርስቲያን ላይ የእጅ ቦምብ በመወርወር በሩ ላይ ጉዳት በማድረስ ወደ ውስጥ ገብተዋል። ቡድኑ ቤተክርስቲያኑ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የአንድ የቄስ ቤት በማቃጠል የቤተክርስቲያኑን የፋይናንስ ኦፊሰር አፍነው ወሰደዋል። ባለፈው ሳምንትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአራቱ የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ የመንግስት ተወካዮችን በነቀምቴ ከተማ በማነጋገር በክልሉ ሰላምና ልማት ስራዎች ላይ መክረዋል።2 ነጋሣ ደሳለኝ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ፣ እሸቴ በቀለ፣ ‘ጠ/ሚ ዐቢይ በነቀምት ከነዋሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት፣’ ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ሚያዚያ 12, 2015 በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው በሚያዚያ 15 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በታንዛኒያ ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ – እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተብሎ ከሚጠራው – ጋር የሰላም ድርድር እንደሚጀመር አስታውቀዋል።3ዳዊት እንደሻው፣ ‘ኢትዮጵያ ከኦኤል አማፂ ቡድን ጋር ድርድር ልትጀምር ነው’ ሮይተርስ፣ ሚያዝያ 15, 2015 በዚህም መሰረት የቡድኑ ተወካዮች እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን በሚያዝያ 17 ቀን መነጋገር ጀምረዋል።4ዳዊት እንደሻው እና ጁሊያ ፓራቪሲኒ፣ ‘በኢትዮጵያ እና በኦሮሞ አማፂ ቡድን መካከል የሚደረገው ውይይት በታንዛኒያ ተጀመረ’ ሮይተርስ፣ ሚያዚያ 17, 2015
በትግራይ ክልል የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ሚያዝያ 11 ቀን በደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞን ደንጎላት በተባለ ቦታ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀላል እና ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከብ ጀምሯል። እነዚህን የጦር መሳሪያዎች የማስረከቡ ሂደት ለቀናት በተለያዩ ካምፖች የሚቀጥል ይሆናል።5የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት፣ ‘የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በደንጎላት የተሰበሰቡ የመጀመሪያ ዙር የተለያዩ የቡድን መሳሪያዎችን ከህወሃት ተረከበ፣’ ሚያዚያ 11, 2015 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትህነግ/ህወሓት ተወካዮች እንዳሉት ከሆነ ይህ ሶስተኛው ዙር የትህነግ/ህወሓት ትጥቅ መፍታት ስነ-ሥርዓት ነው። በመጀመሪያው ዙር ህወሓት ከባድ መሳሪያ ያስረከበ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ፀረ-አውሮፕላን እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን አስረክቧል።6አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘በትግራይ ክልል የጦር መሣሪያ ማሠባሠብ፣’ ሚያዝያ 12, 2015
በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል ባለፈው ሳምንት የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) – የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ሠራዊት እየተባለም የሚታወቀው – ቡድን 195 አባላት መሳሪያቸውን በማስረከብ የትጥቅ ትግል በማቆም ወደ ህብረተሰቡ ለመመለስ የወሰኑ የሽምቅ ታጣቂዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል።7የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘የጋነግ ወደ ሰላማዊ ትግል መመለስ ኢቲቪ | ኢትዮጵያ | ዜና፣’ ሚያዚያ 14, 2015 ጋነግ ከ2013 የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ በኋላ በጥቅምት 2014 የተመሰረተ አዲስ ድርጅት ነው። የምርጫ “ህገወጥ አሰራር እና ብልሹ አሰራርን” በመጥቀስ ቡድኑ ትጥቅ በማንሳት የጋምቤላ ክልል መንግስትን ለማስወገድ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቆ ነበር።8 ኢትዮጵያ አውቶኖመስ ሚዲያ፣ ‘የጋምቤላ ነፃነት ግንባር መቋቋሙን ስለማሳወቅ፣’ ጥቅምት 21፣ 2014 የቡድኑ መሪዎች በህዳር 2014 ከትህነግ/ህወሓት እና ከኦነግ-ሸኔ ጋር መተባበራቸውን አስታውቀው ነበር (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014 ይመልከቱ)። ሰኔ 7, 2014 ጋነግ ከኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በመሆን ጋምቤላ ከተማን ለአጭር ጊዜ ተቆጣጥሮ ነበር። በቡድኑ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች መካከል በደቡብ ሱዳን ጁባ እና አዲስ አበባ ከየካቲት 2015 ጀምሮ የሰላም ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል።9አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- ክልል መንግስት፡ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር በጁባ፣ አዲስ አበባ፣ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ 195 ታጋዮችን ሰላማዊ ፖለቲካ ለመከተል ወደ ሀገር መልሷል’ ሚያዚያ 12, 2015
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሚያዚያ 9 እስከ 11 ቀን ድረስ የወረዳው አስተዳደር ላለፉት 3 ወራት ደመወዛቸውን ባለመክፈሉ ምክንያት የመንግስት ሰራተኞች በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ ጎዳና በመውጣት በድንጋይ እና በዱላ መንገዶችን ዘግተዋል። መንገዶቹ በሚያዚያ 12 ቀን ተከፍተዋል።10የኢትዮጵያ ሚዲያ ስርቪስ፣ ‘ኢኤምስ መረጃ ሐሙስ ሚያዚያ 12, 2015፣’ ሚያዚያ 12, 2015
በመጨረሻም በሱዳን የታተሙ በርካታ ዘገባዎች በአወዛጋቢው አል–ፋሻጋ አካባቢ በሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች እና በኢትዮጵያ ኃይሎች መካከል ውጊያ መከሰቱን ጠቁመዋል።11 አልሱዳኒ ዜና፣ ‘ሠራዊቱ በአል-ፋሻጋ አል-ሱራ ላይ የኢትዮጵያን ወረራ ያስቆመ ሲሆን በሕይወት እና በመሳሪያያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፣’ ሚያዝያ 11, 2015፤ አሻርክ አል-አውሳት፣ ‘”የድንበር ውዝግብን” ለመፍታት ኢትዮጵያ የሱዳንን አለመረጋጋት እየተጠቀመች ነውን?’፣ ሚያዝያ 13, 2015 ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን ክስ ሀሰት ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን በሁለቱ አገሮች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የውሸት ወሬ “ፓርቲዎች” እያስተላለፉ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።12ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ሚያዚያ 12, 2023 በይፋ የሱዳን አካል ቢሆንም ብዙ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበትን13አህመድ ዮነስ፣ ‘ከኢትዮጵያ ጋር ከተስማሙ በኋላ አል-ፋሽጋ ወደ ሱዳን ይመለሳል፣’ አሻርክ አል-አውሳት፣ ሚያዚያ 4, 2012 ይህን አካባቢ የሱዳን ኃይሎች በጥቅምት 2013 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በትግራይ መጀመሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች አካባቢውን ለቀው በወጡበት ወቅት አካባቢውን ተቆጣጥረውታል። በሱዳን በገዳርፍ ግዛት እና በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለው ይህ አለም አቀፍ ድንበር በሁለቱ ሀገራት መካከል በታሪክ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳበት ነው (ለበለጠ መረጃ የኢፒኦን የአል ፋሻጋ የድንበር ግጭት ገፅን ይመልከቱ)። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህ የድንበር ውዝግብ ከሱዳን መንግስት ጋር በሚደረግ ድርድር በሰላማዊ መንገድ እንደሚፈታ ገልፀው በጉዳዩ ዙሪያም የሱዳን ተወካዮችን ማነጋገራቸውን አስታውቀው ነበር።14 ዲደሊው አማርኛ፣ ‘ጥር 14 የዓለም ዜና’፣ ጥር 14, 2014፤ ሱዳን ትሪቡን፣ ‘አል-ቡርሃን ሱዳን የኢትዮጵያን ትህነግ/ህወሓት እንደማደግፍ አህመድን ለማሳመን ታግሏል’፣ ጥቅምት 9, 2014 በሱዳን በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በሚመራው የሱዳን ጦር እና ሃምዲቲ ተብሎ በሚጠራውም በመሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሚመራው ፓራሚሊታሪ ፈጥኖ ደረሽ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት አል-ፋሻጋን ተቆጣጥረውት የነበሩት የሱዳን ወታደሮች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው ተዘግቧል።15ኢኤምስ፣ ‘ኢኤምስ መረጃ ሐሙስ ሚያዚያ 12, 2015፣’ ሚያዚያ 12, 2015