በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት
ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ድረስ አክሌድ 37 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 69 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል። ባለፈው ወር የፖለቲካ ግጭቶች መቀነሳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ህዝባዊ ስልፎች ግን ጨምረዋል።
- ባለፈው ወር በአማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኩነቶች እና በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ሪፖርት የተደረገ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን 26 ኩነቶች እና 47 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግቧል። ከ68% በላይ የሚሆነው በሃገሪቱ ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልል ነው።
- ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም ተደጋግሞ የተከሰተው የኩነት ዓይነት ተቃውሞ ሲሆን 33 የተቃውሞ ኩነቶች ተመዝግበዋል። አብዛኛዎቹ የተመዘገቡት ተቃውሞዎች በአማራ ክልል ሲሆን እነዚህም መንግስት የክልል ልዩ ኃይልን ለመበተን ከያዘው እቅድ ጋር የተያያዙ ነበሩ።
ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
ወርሀዊ ትኩረት፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት
በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ብጥብጥ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ባለው ጊዜ ውስጥም መቀነሱን የቀጠለ ሲሆን አክሌድ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከመጀመሩ በፊት ከመስከረም 2013 ቀጥሎ ዝቅተኛውን የፖለቲካ ግጭት ኩነቶችን በለፈው ወር መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። ሰላምን ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶች የቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ወር በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች እና በመንግስት መካከል ውይይት መደረጉ ተገግሯል። ሆኖም የሀገሪቱ ልዩ ኃይል ወደ ተለያዩ የፀጥታ ማዋቅር እንዲዋሃድ የታቀደው እቅድ በአማራ ክልል ቅሬታን ያስናሳ ሲሆን በዚህም ምክንያት ሰልፎች እና ውጊያዎች በክልሉ ተቀስቅሷል። የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ በወሩ መጨረሻ መገደሉ በአማራ ክልል በቀጣይ ወራቶች የበለጠ መጠነ ሰፊ አለመረጋጋት እንደሚኖር ሊያመላክት ይችላል።
በኢፒኦ ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 22, 2015 ወርሃዊ ሪፖርት ላይ እንደተብራራው በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ከተለያዩ ታጣቂዎች ጋር የሚደረገው የሰላም ድርድር ተስፋን በሚሰጥ መልኩ እየቀጠለ ይመስላል። በሚያዝያ ወር በመንግስት እና እንዲሁም በመንግስት እና በአካባቢው ነዋሪዎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በመባል በሚታወቀው1ኦሮሞዎች የአፋን ኦሮሞ ምህፃረ ቃል የሆነውን አባኦ (ABO- Adda Bilisummaa Oromoo) የሚለውን ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ ቡድኑን ሸኔ ብለው ይጠሩታል። በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የሚደረግ የሰላም ድርድር በታንዛኒያ በይፋ ተጀምሯል።2ቻርለስ ኮምቤ፣ ‘በኢትዮጵያ መንግሥትና በኦኤላኤ መካከል የሚደረገው የሰላም ውይይት በታንዛኒያ ይቀጥሏል፣’ የአሜሪካ ድምፅ፣ ሚያዝያ 19, 2015 በህዳር እና ታህሳስ 2015 ከኦነግ-ሸኔ ጋር የተያያዙ ኩነቶች በከፍተኛ ሆኔታ ከጨመረ በኃላ የአክሌድ የመረጃ ቋት እንደሚያመላክተው ከታህሳስ በኃላ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን ይህም የሰላም ንግግሩ ቀደም ብለው ተጀምሮ ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ ኩነቶች መቀነሱ በጥቅምት 2015 የሰላም ስምምነቱ ከትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ጋር ከተፈረመ በኋላ የፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ለመንቀሳቀስ ከመቻላቸው ጋርም የተያያዘ ሊሆን ይችላል። በተመሳሳይ በሰኔ 2014 ዓ.ም ከኦነግ-ሸኔ ጋር በጋምቤላ ከተማ በጋራ ጥቃት ያደረሰው የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3, 2014 ይመልከቱ) አመራር በሚያዝያ ወር በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎቹን ወደ ተሃድሶ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በማስገባት ቡድኑ “ሙሉ በሙሉ ከትጥቅ ትግል መውጣቱን” አስታውቋል።3ነጋሳ ደሳለኝ፣ ታምራት ዲንሳ፣ ነጋሽ መሀመድ፣ ‘የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሙሉ በሙሉ ከትጥቅ ትግል መውጣቱን ዐስታወቀ፣’ ሚያዝያ 18, 2015
መጋቢት 28 ቀን የኢትዮጵያ መንግስት የእያንዳንዱን ክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ለማዋሃድ እቅድ አንዳለው አስታውቋል።4አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የጦር አዛዡ የክልሉ ልዩ ኃይል “ከዛሬ ጀምሮ” እንደሌሌ አሳወቁ፣’ ሚያዝያ 7, 2015 የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ለክልል መንግሥታት “የክልሉን ፖሊስ ኃይል የማደራጀት፣ የመምራት እና የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስከበር” መብት ይሰጣል።5ኮንስትቲውት ፕሮጀክት፣ ‘የ1987 የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት’ አንቀፅ 52 ልዩ ሃይሎች የተደራጁት በየክልላቸው ድንበሮች ውስጥ የሚነሱትን የሽምቅ ውጊያዎች ለመከላከል ነበር። ነገር ግን ይህ ልዩ ሃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚፈፅሙት ጥቃቶች እና በድንበር ውዝግቦች ላይ በመሳተፈቸው አወዛጋቢ ሆነው ቆይተዋል። እንደ አክሌድ መረጃ ቋት ከሆነ ከ2010 ጀምሮ ከተመዘገቡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ የጥቃት ኩነቶች ወስጥ 18% በሚሆኑት የክልል ልዩ ኃይሎች የተሳተፉበት ናቸው።
የሶማሌ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል (የደቡብ ክልል) ባለስልጣናት የፌዴራል መንግስት መመሪያን ለመከተል ማቀዳቸውን ያስታወቁ ሲሆን የልዩ ኃይልን ከሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ጋር የማዋሃድ ሂደቱን በተወሰነ የህዝብ ምላሽ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።6አዲስ ስታንደርድ፣ ‘ኒውስ አለርት፡ የሶማሌ ክልል ካቢኔ የመንግስትን የክልል ልዩ ኃይል የመበተን የመቀላቀል እቅድን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፣’ ሚያዚያ 2, 2015፤ ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የኦሮሚያ ክልል የልዩ ኃይል አደረጃጀትን ሥምሪት ማቆሙን አስታወቀ፣’ ሚያዚያ 5, 2015 በአማራ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልሉን ልዩ ኃይል ትጥቅ ለማስፈታት አስቧል በሚል በተናፈሰው ወሬ ምክንያት መጋቢት 28 ቀን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በልዩ ኃይሉ እና ልዩ ኃይሉን በሚደግፉ የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች የተቀሰቀሰ ሲሆን በሰሜን ወሎ ዞን በጎቢዬ፣ በቃሊም፣ በላጎ እና ጎማጣ ውጊያዎች ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። እነዚህ ውጊያዎች ከተከሰቱ በኋላ መንግስት ሁሉንም የክልል ልዩ ኃይሎች ከክልል ፖሊስ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ለማዋሃድ ያለውን እቅድ የሚያብራራ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።7የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘በወቅታዊ ጉዳይ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 28, 2015 ይህ መግለጫ በመላው አማራ ክልል ተጨማሪ ውጊያዎችን፣ አመፆችን እና ተቃውሞዎችን አስከትሏል (ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: መጋቢት 23-29, 2015 እና ኢፒኦ ሳምንታዊ: መጋቢት 30-ሚያዚያ 6, 2015ን ይመልከቱ)። በእነዚህ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ቢያንስ 15 ሰዎች ሞቱ ሲሆን አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ተቃዋሚዎችን ለመበተን በተኮሱት ጥይት ምክንያት የተገደሉ ናቸው። ይሁን እንጂ በክልሉ ለአንድ ሳምንት ያህል አለመረጋጋት ከተፈጠረ በኋላ መንግስት የልዩ ኃይሎችን ለማወሃድ ባቀደው እቅዱ ላይ የተለያዩ ማብራሪያዎችን በማውጣቱ8አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘”የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም” ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣’ ሚያዚያ 1, 2015፤ አሚኮ፣ ‘የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ የሰጡት ማብራሪያ፣’ ሚያዚያ 3,2015፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘ከጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተደረገ ቆይታ፣’ መጋቢት 29, 2015 እና ከምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች ጋር በተደረገ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስነስርዓት9አሚኮ፣ ‘በሰሜን ወሎ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ መደበኛ ህይወታቸው ለመመለስ ተስማሙ፣’ ሚያዚያ 5, 2015 በኃላ ሚያዝያ 5 አካባቢ አለመረጋጋቱ ጋብ ብሏል። ነገር ግን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊን እና የፓርቲውን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ከጠባቂዎቻቸው ጋር እና ሌሎች የአካባቢው የአስተዳደር አባላትን በሰሜን ሸዋ ዞን ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ እያሉ በመግደላቸው አለመረጋጋቱ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።10አሚኮ፣ ‘ከአቶ ግርማ የሺጥላ ጋር በጉዞ ላይ የነበሩ ተጨማሪ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፣’ ሚያዝያ 22, 2015
በአማራ ኃይሎች ላይ ያተኮረ አጭር የክልል ልዩ ኃይል ምንነት ማብራሪያ
የክልል ልዩ ኃይል – ልዩ ፖሊስ – በየክልላቸው ያሉ ሽምቅ ተዋጊ ኃይሎችን እንዲዋጉ የተቋቋሙ በክልል ደረጃ የሚገኙ የፓራሚሊታሪ (ታጣቂ) ኃይሎች ናቸው። የመጀመሪያው ክልል ልዩ ኃይል በሶማሌ ክልል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባርን ለመዋጋት እ.ኤ.አ. በ2007 (ማለትም 1999/2000 ዓ.ም) ተቋቁሟል።11ዮሮፒያን ኢንስቲትውት ኦፍ ፒስ፣ ‘ልዪ ኃይል በኢትዮጵያ፣’ ጥቅምት 2014፤ ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘የክልል ልዩ ኃይሎችን የማደራጀት ጅማሬ፣ ሂደት እና አሁን የደረሱበት አቋም፣’ ሚያዚያ 4, 2015 በጊዜ ሂደት በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ልዩ ኃይል ተቋቁሟል። ሁለተኛው የክልል ልዩ ኃይል ያቋቋመው በኦሮሚያ ክልል ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2008 (ማለትም 2000/2001 ዓ.ም) 120 አባላት ያሉት ኃይል ተቋቁሟል።12ዮሮፒያን ኢንስቲትውት ኦፍ ፒስ፣ ‘ልዪ ኃይል በኢትዮጵያ፣’ ጥቅምት 2014 ልክ እንደ ክልል ፖሊስ ሁሉም የክልል ልዩ ኃይል ተጠሪነቱ ለየክልላቸው መንግስት ነው። አደረጃጀታቸው እንደ መከላከያ ሠራዊት ሲሆን እያንዳንዱ ልዩ ኃይል የተለያዩ ደረጃዎችን እና ክፍለ ጦሮችን ያቀፈ ነው።
እንደ ደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ከተለያዩ ብሔሮች የተዋቀሩ ልዩ ኃይሎች ውጪ የኢትዮጵያ ብሔር ተኮር ፌዴራሊዝም ስርዓት የክልል ልዩ ኃይሎች ከአንድ ብሔር የተዋቀሩ በመሆናቸው የይገባኛል ጥያቄ ባለባቸው ቦታዎች እና ድንበሮች ግጭት ውስጥ በመሳተፈቸው እና በአካባቢያቸው የሚገኙ በቁጥር አነስተኛ ብሔረሰቦች አያያዝ ጋር በተያያዘ ችግር ፈጥሯል። ከጊዜ በኋላ እና በተለይም ከ2008 በኋላ የክልል ልዩ ኃይሎች በድንበር ግጭቶች እንዲሁም እርስ በእርስ መዋጋት ጀምረዋል። ለምሳሌ በ2012/13 እና 2013/14 በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የአፋር እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች የተሳተፉባቸው ውጊያዎች ተመዝግበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመጋቢት 2010 ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በተለይ በትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የልዩ ኃይሎች ስልጠና እና ልዩ ኃይሎችን ማስታጠቅ በፍጥነት ጨምሮ ነበር።13ኢቢሲ፣ ‘የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይል ፖሊሶች አስመረቀ፣’ ሚያዚያ 2, 2013፤ ኢቢሲ፣ ‘የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን አስመረቀ|etv፣’ የካቲት 30, 2012፤ አሚኮ፣ ‘የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ግንባታ ቢሮ ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት አስመረቀ፣’ ሰኔ 10, 2011፤ ትግራይ ቲቪ፣ ‘#ቴሌቪዥን_ትግራይ፡“ትግላችን አጭርና መራራ ነው፡፡”የተመረቁ የትግራይ ልዩ ኮማንዶች፣’ ጥቅምት 9, 2013 ይህ የትጥቅ እሽቅድድም በፌዴራል ኃይሎች ላይ እምነት ከማጣት እና የክልል ባለስልጣናት ክልሎቻቸውን ከአጎራባች ኃይሎች ሊደርስ የሚችለውን የግዛት ወረራ ለመከላከል ካላቸው ፍላጎት ጋር የተያያዘ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የክልሉ ልዩ ኃይሎች አቅም እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳዩ ሶስት አበይት ክስተቶች ተከስተዋል። በሐምሌ 2010 ዓ.ም አብዲ መሀሙድ ኡመርን እንዲሁም አብዲ ኢሌይ በመባል የሚታወቀውን የሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ለማሰር የፌዴራል ኃይሎች ወደ ሶማሌ ክልል ጅግጅግጋ ሲገቡ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ጋር ተጋጭተው ነበር።14አንዱአለም ሲሳይ፣ ‘የኢትዮጵያ ጦር የሶማሌ ክልልን ፀጥታ ተቆጣጠረ፣’ ዘ ኢስትአፍሪካን, ነሐሴ 1, 2010 በአማራ ክልል በሰኔ 2010 ዓ.ም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትንእና ሌሎች እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጥተዋል የተባለ ሲሆን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊው ከቀናት በኋላ በፌዴራል ፖሊስ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል። ይህም ለኃላፊ ታማኝ በሆኑ የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ውጊያ አስከትሎ ነበር። በመጨረሻም በጥቅምት 2013 ዓ.ም በትህነግ/ህወሓት የሚመራ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ኮማንድ ፖስት ላይ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን ይህም በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የዘለቀ ጦርነት አስከትሏል።
በአማራ ክልል የታጠቁ አካላት፡ በአማራ ብሔርተኝነት ስር ያለ አንድነት
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በአማራ ክልል ውስጥ የሚደረጉ የሸምቅ ውጊያ ሙከራዎችን በተለይም የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር የሚፈልጉ ብሔርተኛ ቡድኖችን በመቆጣጠር ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። ከትህነግ/ህወሓት በተጨማሪ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ከኦሮሞ ብሔር ታጣቂዎች እና ከኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጋር፣ በጎንደር ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ የቅማንት ታጣቂዎች ጋር፣ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በክልሉ ምስራቅ አካባቢ ከሚገኙ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ሲያካሂድ ቆይቷል። ከአማራ ክልል ውጪ የአማራ ክልል ኃይሎች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል – ብዙ የአማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ በመተከል ዞን15አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና ትንተና፡- የአማራ ክልል ጦሩን ወደ አጎራባች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሰማራ፣ እርምጃው በቅርቡ በታጠቁ አማፂያን የፀጥታ ኃይሎች ከተገደሉ በኃላ የተደረገ ነው፣’ መስከረም 3, 2014 – በሱዳን ድንበር እና በሰሜን በነበረው ግጭት በትግራይ ክልል በተከሰቱ ውጊያዎች ተሳትፈዋል። እንደሌሎች ክልል ልዩ ኃይሎች ሁሉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በእነዚህ የፀረ-ሽምቅ ዘመቻዎች ወቅት የተለያዩ ከባድ ወንጀል በመፈፀም ተከሰዋል። በታህሳስ 2014 የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን 30 የኦሮሞ ተወላጆችን ከኦነግ-ሸኔ ጋር ተባብረዋል በሚል ከህግ አግባብ ውጪ ሲገድሉ ያሚያሳይ ቪዲዮ ተቀርጾ ነበር።16ቢቢሲ፣ ‘የኢትዮጵያ ግጭት፡ በተረሳ የእልቂት ቪዲዮ ውስጥ ፍንጭ መፈለግ፣’ ጥቅምት 28, 2015 በመስከረም 2013 የአማራ ክልል ኃይሎች እና “ከመደበኛ ውጪ ያሉ ኃይሎች” በትግራይ ተሳትፈዋል በሚል በዩናይትድ ስቴትስ በተጣለው የነፍስ ወከፍ ማዕቀብ በተለይ ኢላማ ተደርገው ነበር።17ዋይት ሀውስ፣ ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ቀውስን በተመለከተ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ለመጣል የወጣ አስፈፃሚ ትዕዛዝ፣’ መስከረም 7, 2014
በተጨማሪም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በትግራይ ክልል የአማራ ተወላጆች በብዛት የሚገኙበትን ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ እና ራያ አካባቢዎች በመያዝ እና በመቆጣጠር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ኮማንድ ፖስትን በመርዳት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። የልዩ ኃይል ክፍሎቹ ‘ከፋኖ’ ታጣቂዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ የነበረ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች በምዕራብ ትግራይ ዞን በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ የጦር ወንጀል በመፈፀም ይወነጀላሉ።18አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ‘“ከዚች ምድር እናጠፋችኋለን”፡ በኢትዮጵያ ምዕራብ ትግራይ ዞን በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና የዘር ማጥፈት፣ መጋቢት 28, 2014
ከመደበኛው አደረጃጀት ውጪ ብዙም ካልተደራጁት እና ለአደራጃቸው አካባቢ ታማኝ ከሆኑት ከፋኖ ታጣቂዎች በተለየ መልኩ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ ክልል ፖሊስ የሚታዘዙት ለክልሉ ፕሬዝዳንት ታማኝ በሆኑ መኮንኖች እና በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ባለስልጣናት ነው። ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ አራት የተለያዩ አመራሮች የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በኃላፊነት መርተዋል። የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትን ግድያ አስተባብረዋል የተባሉት ጄኔራል አሳምነው ጽጌ በ2011 ዓ.ም ሊያመልጡ ሲሉ በፀጥታ ኃይሎች ከተገደሉ በኃላ ምክትል ኮሚሽነር ብሰት ጌታሁን በእሳቸው ምትክ የክልል ልዩ ኃይሉን እስከ ሐምሌ 2013 በኃላፊነት መርተዋል። ከሐምሌ 2013 ጀምሮ ከስልጣን እስከተነሱበት ጥር 2014 ዓ.ም ድረስ ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ ልዩ ኃይሉን በኃላፊነት መርተዋል። በኃላ ላይ በግንቦት 2014 ዓ.ም በሽበርትኝነት ተከሰው በፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ታስረው ነበር።19ቦርከና፣ ‘የታፈኑት የኢትዮጵያ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ተፈቱ፣’ ሰኔ 5, 2014 ሜጄር ጄኔራል መሰለ በለጠ ልዩ ኃይሉ በዚህ ወር እስከፈረሰበት ድረስ ልዩ ኃይሉን በኃላፊነት መርተዋል።
ፋኖ ብዙውን ጊዜ ወጣቶችን ያቀፈ የአማራ ብሔር ተወላጆችን የመጠበቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው የአካባቢ ታጣቂዎችን የሚያመለክት ቃል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሌሎች ብሔር ተኮር ታጣቂዎች በተለየ መልኩ በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ ፋኖዎች በጣም የተሳሰሩ እና የኢትዮጵያ አንድነትን እና የምዕራብ እና የደቡብ ትግራይ ዞኖች አካባቢዎችን ጨምሮ በታሪክ የአማራ መሬት ናቸው በሚባሉ ቦታዎች ሁሉ የአማራ አስተዳደር እንዲመለስ የሚሟገቱ ናቸው። ፋኖዎች በአካባቢው ማህበረሰብ የሚደደገፋ ሲሆኑ አመራሩ ብዙውን ጊዜ የቀድሞ የክልል ወይም የፌዴራል ታጣቂ አባላትን ያካትታል።
ከትህነግ/ህወሓት ጋር በነበረው ግጭት በአማራ ክልል ከጦርነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለማተኮር በጀቱን ጨምሮ መደበኛ አገልግሎት ተቋርጦ ነበር።20አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘በአማራ ክልል ምክር ቤት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዘጠኙ ነጥቦች ትርጉም፣’ ጥቅምት 18, 2014 ይህም በመላው ኢትዮጵያ እና በዲያስፖራ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በመመልመል እና በማስታጠቅ ብዙዎቹ ከፋኖ ታጥቂዎች ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጎ ነበር።21የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ‘ከአሜሪካ ለህልውና ትግል ደሴ የገቡት ፋኖዎች፣’ ጥቅምት 15, 2014 በዚህ ጊዜ ፋኖ እንደ ድርጅት የተለያዩ የአካባቢ አዛዦችን እና ድርጅታዊ መዋቅሮችን በማወጅ የበለጠ መደበኛ አደረጃጀትን ያዘ። በሀገሪቱ ግጭት እየቀነሰ በመምጣቱ በአማራ ክልል መንገዶች እና ከተሞች የሚዘዋወሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች ከፋኖ ታጥቂዎች ጋር አልፎ አልፎ የተዋጉ ሲሆን ይህም ሊመጣ የሚችለውን ማዕበል አመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ቅርንጫፍ የተወከለው በፌዴራል መንግሥት እና ፋኖ መካከል የተፈጠረው መቃረን ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው። በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲሁም በኦሮሚያና በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልሎች የአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የፌዴራል መንግስት እርምጃ ባለመወሰዱ በፌዴራል መንግሥትና በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ላይ ቁጣ ቀስቅሷል። በተመሳሳይ መልኩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በመንግስት ላይ የበላይነት እየያዙ ነው የሚለው አስተሳሰብ ብዙ የፋኖ አባላት አሁን ያለው አስተዳደር የአማራን ጥቅም ለማስጠበቅ ፍቃደኛ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል።22ሄኖክ አበበ፣ ‘አብይ አህመድ በአማራ የወሰደው የበቀል እርምጃ፡ የሚያበላውን እጅ መንከስ’ ቦርከና፣ ሚያዝያ 9, 2015 ከሌላ ክልል ኃይሎች ወይም ከፌዴራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ የፋኖ አባላት በመንግስት ‘ፅንፈኞች’ ይባላሉ።23አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የኦሮሚያ ክልል ወደ ክልሉ እየገቡ ‘አጸያፊ ድርጊቶችን’ እየፈጸሙ ‘በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎችን’ አስጠነቀቀ፣’ መጋቢት 26, 2014 ብዙ ጊዜ ከትህነግ/ህወሓት ጋር በነበረው ግጭት ጎን ለጎን ቢፋለሙም በ2014 ዓ.ም ለአማራ ብልፅግና ፓርቲ ታማኝ የሆኑ የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የፋኖ ታጥቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ባደረጉት ሙከራ ግጭት ገጥሞቸው ነበር።
በብሔርተኛ ድርጅቶች የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል ችላ በማለት እና የኦሮሞ አጀንዳን በማስፈፀም በሚወነጀለው በብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት የሚመራው የፌዴራል መንግስት ምክንያት የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።24አልጀዚራ፣ ‘የእርዳታ ቡድን በኢትዮጵያ አማራ ክልል ሁለት ሰራተኞች በጥይት ተመተው መገደላቸውን ገለጸ፣’ ሚያዝያ 2, 2015 መንግስትን ከትህነግ/ህወሓት እና ከኦነግ-ሸኔ ጋር በሚያደርገው የሰላማዊ ድርድር በአማራ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው በደል ተጠያቂነትን በሚያስወግድ መልኩ እና ልዩ ኃይሉን ትጥቅ በማስፈታት የአማራ ክልልን መከላከያ አልባ አድርጎታል ብለው የሚከሱ የአማራ ብሔርተኛ ድምጾች እየጨመሩ መጥተዋል።25ትዊተር @ሲደሳለኝ፣ መጋቢት 14, 2015፤ አቤል ተስፋዬ፣ ‘የኢትዮጵያ ጥምረት መቀየር፣ የአብይ ሲመተ በአል ቀን በአማራ ተቃውሞ እና ግጭት ተከሰተ፣’ ኢትዮጵያ ኢንሳይት፣ መጋቢት 29, 2015 ለምሳሌ በሚያዚያ 2013 ዓ.ም ከኦሮሚያ፣ ከአማራ እና ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልሎች አከባቢዎች በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን የኃይል ጥቃት እና መፈናቀል በመቃወም በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ህዝባዊ ሰልፎች ተካሂደው ነበር (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሚያዚያ 9, 2013 እስከ ሚያዚያ 15, 2013 ይመልከቱ)።
በአሸዋ ላይ የተሰመሩ መስመሮች፡ በአማራ ክልል ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች
የአማራ ክልል በመንታ መንገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የታጠቁ አካለት ቁልፍ ቦታዎችን ለመያዝ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት አልፎ አልፎ የሚከሰተው ውጊያ ሊቀጥል የሚችልበት አዝማሚያ ከፍተኛ ነው። በትህነግ/ህወሓት እና በፌዴራል መንግስት መካከል ያለው ግጭት በማብቃቱ ፋኖን እና የፌዴራል መንግስት ኃይሎችን አንድ ያደረጋቸው የጋራ ጠላት አብሮ አብቅቷል። በአማራ ብልፅግና ፓርቲ እና እንደ ፋኖ ባሉ በአማራ ክልል በሚገኙ ብሔርተኛ ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት በፍጥነት እያሽቆለቆለ መጥቷል። በግንቦት 2014 ዓ.ም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በተለያዩ የክልሉ ከተሞች የአካባቢ የፋኖ አመራሮችን ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ የሰው ህይወት የቀጠፈ ውጊያ እንዲቀሰቀስ አድርጎ ነበር (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 6 እስከ 12, 2014 ይመልከቱ)። በሚያዚያ 2015 ዓ.ም የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ ከታወጀ በኋላ የተከሰተው ውጊያ ከአንድ አመት በፊት የተከሰቱትን ኩነቶች የሚያንፀባርቁ ናቸው።
በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች የልዩ ኃይል መልሶ ማዋቀሩ ዜና ብዙም ተፅዕኖ አልፈጠረም። ነገር ግን የክልሉ ልዩ ኃይል መበተን ዜና በአማራ ክልል የአማራ ድምጽ የሆኑትን ስልጣን ለመቀነስ እና የፌዴራል መንግስትን ፍላጎት ለመጫን የተደረገ ሙከራ ተደርጎ ተወስዷል። ፓን-ኢትዮጲያውያን እና የአማራ ክልል የፖለቲካ አካላት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እና የገዢውን የብልጽግና ፓርቲን የኦሮሞ ብሔር የፖለቲካ ጥያቄዎች በማስተናገድ እና እነዚህን ጥያቄዎች በመንግስት ላይ የበላይ እንዲሆኑ አድርገዋል ሲሉ በስፋት ይከሷቸዋል።26 ቦርከና፣ ‘አዎ! አብይ አህመድ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው፣ መጋቢት 27, 2015 የልዩ ኃይል ትጥቅ ማስፈታቱ በይፋ የትግራይ ክልል አካል ቢሆኑም በታሪክ ከአማራ ብሔር ጋር ትስስር ያላቸው እና በ2013 ዓ.ም የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል ባለስልጣናት የሚተዳደሩተን የወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ እና ራያ አካባቢዎች የፌዴራል መንግስት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ አካባቢዎች ፀጥታ በማስከበር የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን እነዚህን ኃይሎች ወደ ፌዴራል ጦር ወይም የክልል ፖሊስ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ከትህነግ/ህወሓት ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ስምምነት በመቃወም ሊነሳ የሚችል የትጥቅ ተቃውሞን ያስወግዳል። ይህ አቋም በርካታ የአማራ ደጋፊ ጋዜጠኞችን እና አክቲቪስቶችን ለእስር ዳርጓል።27አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ‘ኢትዮጵያ፡ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሊያከብር እና የታሰሩትን የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ ይፍታ’ ሚያዝያ 9, 2015፤ ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስት፣ ‘በኢትዮጵያ በድጋሚ በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ቢያንስ 8 ጋዜጠኞች ታስረዋል፣’ ሚያዝያ 6, 2015
የአሁኑ የአማራ ክልል ሁኔታ በሐምሌ 2006 ዓ.ም በጎንደር የወልቃይት ኮሚቴ መሪ የነበረውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ግጭት ካስከተለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት አለው። የአማራ ብሔርተኝነት ላይ የሚያተኩሩ ባለሙያዎች ፋኖ እንዲመሰረት ያደረገውን እና በኋላም ውስን ጸረ-መንግስት የትጥቅ እንቅስቃሴዎችን ያስከተለውን ይህንን በጎንደር የተከሰተውን ሁኔታ “የአማራ ብሔርተኝነት የቀየረ ነው” ብለው ይመለከቱታል።28ተዘራ ታዘበው፣ ‘የአማራ ብሔርተኝነት፡ የኢምፓየሩ መልስ፣’ አፍሪካን አፌርስ፣ ጥር 12, 2013 በ2011 ዓ.ም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በሆኑ ብሔርተኛ ኃይሎች የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አምባቸው መኮንን ለሞት የዳርገውን በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ሁለተኛው ለውጥ ያመጣ ክስተት ነው። ባለፈው ወር የአማራ ብልፅግና ፓርቲ መሪ መገደል ለአማራ ጽንፈኛ ብሔርተኝነት ሦስተኛው ወሳኝ ነጥብ ሊሆን የሚችል ሲሆን ምክንያቱም የተለያዩ አካላትን ይባስ የሚያቃርን እና ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ የሚችል የፀረ-መንግስት ሽምቅ ውጊያ መጀመሪያ ሊሆን ስለሚችል ነው።
የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ላይ ለተፈጸመው ግድያ መንግስት በ”ፅንፈኛ ኃይሎች” ላይ “የማያዳግም እርምጃ” መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።29አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የጋራ ግብረ ሃይል የባለስልጣኑን ግድያ ተከትሎ በአማራ ክልል “አክራሪ ሃይሎች” ላይ “የማያዳግምእርምጃ” እየተወሰደ ነው አለ፣’ ሚያዚያ 20, 2015 በአሁኑ ወቅት ግልጽ ባይሆንም እነዚህ እርምጃዎች በመላው የአማራ ክልል የፋኖ አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ትጥቅ የማስፈታት እና ማሰር እንዲሁም የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎችን የማፍረስ ሂደት መጨረስን ሊያካትት ይችላል።30አሚኮ፣ ‘ልዩ ኀይሎችን መልሶ የማደራጀቱ ሥራ እየተጠናቀቀ ነው፣’ ሚያዚያ 7፣ 2015 በሚያዚያ 22 ቀን በኢትዮጵያ ያለው የፌዴራል ፖሊስ በክልሉ 47 “ጽንፈኛ ኃይሎች” በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግሮ ነበር።31የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ‘ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ፣’ ሚያዚያ 22፣ 2015
በምዕራብ ትግራይ ዞን የሚገኘውን ወልቃይትን ወይም በደቡብ ትግራይ ዞን ያለውን ራያን ከአማራ አስተዳደር ውጪ ለሌላ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ሙከራ ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።32አሚኮ፣ ‘የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልዕክት፣’ ሚያዚያ 10, 2014 ብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች መረጋጋት እያሳዩ በሚቀጥሉበት ወቅት የአማራ ክልል ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ እያስተናገደ ሊቀጥል ይችላል። መንግሥት በበኩሉ ብሔር ተኮር የአማራ አካላትን ትጥቅ በማስፈታት ሥልጣኑን ለማጠናከር የሚያደርገውን ጥረት ሊቀጥል የሚችልበት አዝማሚያ ከፍ ያለ ሲሆን ይህ ደግሞ ተጨማሪ ውጊያዎችን/ግጭቶችን ሊያስከትል ይችላል።