ኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጳጉሜ 4, 2015- መስከረም 4, 2016
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ጳጉሜ 4, 2014- መስከረም 4, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,157
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4,027
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 1,803
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ጳጉሜ 4, 2015- መስከረም 4, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 32
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 70
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 50
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ግጭት የቀጠለ ሲሆን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በኦሮሚያ ክልል ለአጭር ጊዜ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው ውጊያ ባለፈው ሳምንት በፌዴራል ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ መካከል እንደገና ቀጥሏል።
በአማራ ክልል ባለፈው ሳምንት አክሌድ 18 የጦርነት፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት እና የርቀት ጥቃት ክስተቶችን መዝግቧል። በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ ከፍተኛ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን በመስከረም 3 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች ከተማውን ለአጭር ጊዜ ተቆጣጥረው ነበር። የጦርነት ኩነቶች በደቡብ ጎንደር ዞን መካነ እየሱስ ወረዳ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ እና አንጾኪያ ወረዳዎች፣ በሰሜን ወሎ ዞን ጎብዬ፣ ቆቦ ሮቢት እና ወልዲያ ከተሞች እና በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳም ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አክሌድ ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ቢያንስ 39 ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር መዘግቧል። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ የሞቱት በሰሜን ሸዋ ዞን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በፈጸሙት ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ ጋር የተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ በአማራ ክልል በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ሌላ ዙር ጦርነት በክልሉ ከተቀሰቀሰ በኋላ ከህግ አግባብ ውጭ ያለ ግድያ እና እስራት ሁለት እጅግ አሳሳቢ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጿል2የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ‘አማራ ክልል:- ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣’ መስከረም 4, 2016 (በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ዝርዝር ትንታኔን ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 25, 2015ን እና የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2015ን ይመልከቱ)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል ለአጭር ጊዜ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው ውጊያ ባለፈው ሳምንት እንደገና ተቀስቅሷል። በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ፣ በቾ እና ሰደን ሶዶ ወረዳዎች በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት በመሰንዘራቸው ከፖሊስ ኃይሎች ጋር ተዋግተዋል። ይህ ታጣቂ ቡድን አባላቱን ለማስለቀቅ መስከረም 1 ቀን በኢሉ ወረዳ በተጂ ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። በተመሳሳይ ቀን በበቾ ወረዳ ቱሉ ቦሎ ከተማ ቡድኑ ሁለት ፖሊሶችን ከገደለ በኋላ በትንሹ 10 እስረኞችን አፍኖ ወስዷል።3ኢዮብ ተስፋዬ፣ ‘በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ጥቃት የፖሊስ አባላት መገደላቸው እና 10 ንጹሃን መታገታቸው ተገለጸ፣’ አዲስ ማለዳ፣ መስከረም 3, 2016 የፋኖ ታጣቂዎችም በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ኢንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው የተገለጸ ሲሆን መስከረም 4 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች ለቀብር ሥነ-ስርዓት ሲሄድ የነበረ አውቶብስ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገድለዋል (በምስራቅ ወለጋ ዞን በአማራ እና በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች መካከል ስላለው ግጭት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015ን ይመልከቱ)። በግንቦት 2015 በኦሮሚያ ክልል ዳግም ግጭት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በክልሉ የፖለቲካ ግጭት በከፍተኛ ደረጃ እየተከሰተ ይገኛል (በኦሮሚያ ክልል የሰላም ድርድር ከተሞከረ በኋላ ዳግም ስላገረሸው ግጭጥ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23, 2015ን ይመልከቱ)።
በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ የደቡብ ትግራይ ዞን ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መስከረም 1 ቀን የኢትዮጵያን አዲስ አመት ሲያከብሩ ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ በጥይት ተገድለዋል። የግድያው ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን ይህን ድርጊት ፈጽሟል የተባለ አንድ ተጠርጣሪ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።4ዋዜማ ሬዲዮ፣ ‘ለቸኮለ ማለዳ! ሰኞ መስከረም 7/2016 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች፣’ መስከረም 7, 2016 በጳጉሜ 1, 2015 ዓ.ም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ መንግስት በክልሉ ያለውን ግጭት የመቆጣጠር አቅሙ የቀነሰው በጊዜያዊ መንግስት ውስጥ በሚገኝ ማንነቱ ያልታወቀ የተደራጀ ቡድን መሆኑን ገልፀዋል5ትግራይ ቲቪ፣ የጊዜያዊ የትግራይ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣’ ጳጉሜ 1, 2015 (ለበለጠ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ ነሐሴ 27-ጳጉሜ 3, 2015ን ይመልከቱ)።
ጳጉሜ 4, 2015 ዓ.ም. ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሱሪ ወረዳ የመጡ የሱርማ ብሄረሰብ ታጣቂዎች ወደ አጎራባች ጋምቤላ ክልል በመግባት በዲማ ወረዳ በናምካዶ ቀበሌ 12 የወርቅ ማዕድን አውጪዎችን ተኩሰው ገድለዋል። በዚሁ አካባቢ ማንነታቱ ያልታወቀ ሰው አንድ የሱርማ ተወላጅን ከገደለ በኋላ ታጣቂዎቹ የወርቅ ማዕድን አውጭዎቹን በጥይት ተኩሰው መግደላቸው ተዘግቧል።6ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘የአለም ዜና፣ ጳጉሜ 6, 2015፣’ ጳጉሜ 6, 2015
በመጨረሻም በሶማሌ ክልል በቆራሄ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ የጎሳ ታጣቂዎች ተጋጭተዋል። ክስተቱ ቀደም ሲል ከተፈጸመው ክስተት ጋር ተያይዞ የተፈጸመ የበቀል ግድያ መሆኑ ተነግሯል።