በቁጥር: ኢትዮጵያ, መስከረም 5, 2015- መስከረም 11, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,182
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4,030
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 1,721
በቁጥር: ኢትዮጵያ, መስከረም 5, 2016- መስከረም 11, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 46
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 162
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 44
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ የፖለቲካ ጥቃት ቀጥሏል። አብዛኛዎቹ የጦርነት ኩነቶች – 26 – የተመዘገቡት በአማራ ክልል ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በስምንት የጦርነት ኩነቶች ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)።
በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሦስት ዞኖች – ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች – ተዋግተዋል (በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 25, 2015ን፣ የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24, 2015ን እና የኢፒኦ ሳምንታዊ: ሐምሌ 22-28, 2015 ይመልከቱ)። በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢው ለአምስት ቀናት ተዋግተዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች በደምበጫ ከተማ፣ በፍኖተ ሰላም ከተማ፣ በማንኩሳ እና በጅጋ ተዋግተዋል። ሁለቱ ወገኖች በሰሜን ሸዋ ዞንም በራሳ እንዲሁም በአንኮበር እና በሸዋ ሮቢት ከተሞች ተዋግተዋል። የፋኖ ታጣቂዎች ደብረ ማርቆስን እና ደምበጫ ከተማን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ከተዋጉ በኃላ መቆጣጠራቸው ተነግሯል።
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰው አልባ አውሮፕላን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ተዘግበዋል። መስከረም 6 ቀን በደምበጫ እና በፍኖተ ሰላም ከተሞች እና በቋሪት ወረዳ ባልታወቀ ቦታ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን በደምበጫ ቢያንስ 18 ሰላማዊ ሰዎች፣ በፍኖተ ሰላም አንድ እና በቋሪት ወረዳ 30 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።2የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ፣ ‘ ኢኤምኤስ እለታዊ ሰኞ 7 መስከረም 2016፣’ 7 መስከረም 2016 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ ወረዳ ፋኖ ታጣቂዎች ይገኙባቸዋል የተባሉ መንደሮች ላይ በርካታ መድፍ ተኩሷል።
በተጨማሪም መስከረም 6 ቀን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ላይ በምትገኘው አውራ ጎዳና (ቆርኬ) ከተማ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎች ከፋኖ እና ከአማራ ብሄር ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው የኦሮሚያ ክልል ኃይሎች ከተማዋን የአማራ ክልል አካል አድርጎ የሚያሳይ ምልክት ካነሱ በኋላ ነው። ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውና 28 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። በግጭቱ ምክንያት ከ2,000 በላይ ሰላማዊ ሰዎች አካባቢውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።3ሥዩም ጌቱ፣ አዜብ ታደሰ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ፣ ‘የፈንታሌ እና ምንጃር ሸንኮራ አዋሳኝ ግጭት፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ 8 መስከረም 2016 የአውራ ጎዳና ከተማ በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ስር የምትተዳደር ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መካከል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባት ስፍራ ነች (በዚህ አካባቢ ከዚህ በፊት ስለነበረ ግጭት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከመጋቢት 17, 2014 እስከ መጋቢት 23, 2014ን ይመልከቱ)። አንድ የከተማዋ ነዋሪ የፋኖ ታጣቂዎች በአካባቢው አሉ የሚለውን ያስተባበሉ ሲሆን ግጭቱ የጀመረው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወደ ከተማዋ ከገባ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በግጭቱ መሳተፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።4መለስካቸው አምሃ፣ ‘በሰሜን ሸዋ ዞን የአውራ ጎዳና መንደር ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ነዋሪዎች ገለፁ፣’ 8 መስከረም 2016፤ ሥዩም ጌቱ፣ አዜብ ታደሰ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ፣ ‘የፈንታሌ እና ምንጃር ሸንኮራ አዋሳኝ ግጭት፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ 8 መስከረም 2016፤ ኢኤምኤስ፣ ‘ኢኤምኤስ መረጃ ሰኞ 7 መስከረም 2016፣’ 7 መስከረም 2016 ነገር ግን እንደ መንግሥት ከሆነ ሁሉም የክልል ኃይሎች በሚያዝያ 2015 ሕልውናቸው አክትሟል።5 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት፣ ‘ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣’ 7 ሚያዚያ 2015
በአውራ ጎዳና ከተማ ከተፈጠረው ግጭት በተጨማሪ አክሌድ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ቢያንስ ሶስት የውጊያ ክስተቶችን ባለፈው ሳምንት መዝግቧል። በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ አቡ ሸሪፍ ቀበሌ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ቀበሌ ታጣቂዎች ከሶማሌ ክልል ፖሊስ እና የሶማሌ ቀበሌ ታጣቂዎች ጋር መስከረም 6 ቀን ተዋግተዋል። ውጊያው የጀመረው የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች በባቢሌ ከተማ የግብር መስብሰቢያ ቦታ ማዘጋጀት ሲጀምሩ ነው። የፌዴራል ፖሊስና የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ከተማው በመግባታቸው በከተማው የነበረው ውጊያ በቁጥጥር ስር ቢውልም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጊያ በባቢሌ ወረዳ በባቢሌ እና በቦምባስ ከተሞች መካከል በሚገኘው ቆሎጂ አካባቢ ተዛምቷል። ይህ አካባቢ በ2009 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2017) በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረ አለመረጋጋት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ወደ 36,000 የሚጠጉ የሶማሌ ብሔር የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ያስተናግዳል።6ዮናስ አማረ፣ ‘በባቢሌ በኦሮሚያና በሶማሌ ኃይሎች መካከል ግጭት መደረጉ ተሰማ፣’ ሪፖርተር፣ 9 መስከረም 2016፤ አይኦኤም የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ክልላዊ ጽህፈት ቤት፣ ‘አይኦኤም፣ አጋሮች 1,200 የሚጠጉ የተፈናቀሉ ቤተሰቦችን ከኢትዮጵያ ትልቁ የተፈናቀሉ ቦታዎች በፈቃደኝነት ማዛወር ጀመረ ፣’ መስከረል 27 ቀን 2015 በተፈናቃይ ጣቢያው በተፈጠረው ውጊያ በትንሹ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። የባቢሌ ወረዳ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ተፈናቃዮቹ ወደ ባቢሌ ገብተው የእርሻ መሬቶችን እንዲቆጣጠሩ የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች አበረታተዋል ሲሉ ከሰዋል።7ዮናስ አማረ፣ ‘በባቢሌ በኦሮሚያና በሶማሌ ኃይሎች መካከል ግጭት መደረጉ ተሰማ፣’ ሪፖርተር፣ 9 መስከረም 2016