በቁጥር: ኢትዮጵያ, መስከረም 26-ጥቅምት 3, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 27
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 43
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 8
በቁጥር: ኢትዮጵያ, መስከረም 26, 2015-ጥቅምት 3, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,178
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 3,685
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 1,532
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
አማራ ክልል ከአንድ ሳምንት መረጋጋት በኃላ ባለፈው ሳምንት ግጭት ተመልሶ የቀጠለ ሲሆን በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ብዙ ህይወት የቀጠፈ ውጊያዎች ሲዘገብ በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል።
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በቆቦ፣ ወልዲያ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደምበጫ፣ ምንጃር፣ መህር እና ባህርዳር ከተሞች ተዋግተዋል (በአማራ ክልል ስላለው ግጭት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 25, 2015ን ይመልከቱ)። በባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሐምሌ 28, 2015 ከታወጀ በኋላ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በነዋሪዎች ላይ አዲስ የሰዓት እላፊ የጣለ ሲሆን ይህም በከተማዋ እየጨመረ ካለው ግጭት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። በአማራ ክልል ባለፉት ሁለት አመታት የተከሰቱት ግጭቶች እና የሰዓት እላፊ እገዳዎች በንግድ ስራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ ለኢኮኖሚያዊ ችግሮች መባባስ ምክንያት ሆኗል።2ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘ጣና ፍሎራ የአበባ ልማት ድርጅት በግጭቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማጣቱን ገለፀ፣’ ጥቅምት 2, 2016 በተጨማሪም በክልሉ ያለው የድርቅ ሁኔታ “በበርካታ ዞኖች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን” እየጎዳ ይገኛል።3የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ዩኤንኦሲኤቻኤ)፣ ‘የኢትዮጵያ ሁኔታ ሪፖርት፣’ መስከረም 28, 2016
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛው ውጊያ የተከሰተው በሰሜን ሸዋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ነው (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኦነግ-ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ 16 ቀበሌዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን ይህም አንዳንድ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አድርጓል።4አዲስ ማለዳ፣ ‘ኦነግ ሸኔ በደራ ወረዳ 16 የገጠር ቀበሌዎችን መቆጣጠሩ ተገለጸ፣’ መስከረም 29, 2016 በሰሜን ሸዋ ዞን ከተፈጠረው ውጊያ በተጨማሪ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የ12 ሰዎች ህይወትን የቀጠፈ በኦነግ-ሸኔ ላይ እንዳነጣጠረ የተገመተ የአየር ጥቃትን ጨምሮ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን ተዘግቧል። በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኦነግ-ሸኔ ላይ የሚወሰደው የአየር ድብደባ ከዚህ ቀደም ለብዙ ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት መጥፋት እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወቀሳ አስከትሏል።5ሮይተርስ፣ ‘የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል የአየር ድብደባ በመፈጸም ተከሰሰ’፣ ጥቅምት 17, 2015
በአፋር ክልል ብዙም ያልተለመደ የተቃውሞ ስልፍ የተደረገ ሲሆን ከ500 በላይ ወጣቶች በበርሀሌ ከተማ የመልካም አስተዳደር እጦት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን በክልሉ የታሰሩ ወጣቶች እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የተቃዋውሞ ስልፈኞቹን “ሰላም ፈላጊ አይደሉም” ሲሉ ከሰዋል።6ልደት አበበ እና እሸቴ በቀለ፣ ‘ጨው እና ወርቅ ላይ ተኝተን በርሃብ እየሞትን ነው፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥቅምት 2, 2016 የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በሰልፉ ላይ የተለያዩ ምስሎችን ይዘው የታዩ 10 ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋቸው ተነግሯል።
በተጨማሪም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በቀቤና ልዩ ወረዳ እና በወልቂጤ ከተማ መካከል በተፈጠረ የወሰን ውዝግብ ምክንያት በጥቅምት 2 ቀን ወልቂጤ ከተማ ውስጥ በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰቦች ሁከት ፈጣሪዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሷል። በሁከቱ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል።7ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘በወልቂጤ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ፣’ ጥቅምት 5, 2016 ባለስልጣናቱ በከተማው ውስጥ የእንቅስቃሴ ገደብ የጣሉ ቢሆንም በሳምንቱ መጨረሻም ሁከቱ ቀጥሏል። በቅርቡ የተቋቋመው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞንን በሦስት የአስተዳደር እርከኖች የከፈለ ሲሆን የምስራቅ ጉራጌ ወረዳ ራሱን የቻለ ዞን እንዲሆን እና የቀቤና እና ማረቆ ወረዳዎች ደግሞ ልዩ ወረዳ ሆነው እንዲደራጁ ወስኗል። ከዚህ ውሳኔ በኃላ በወሰን ውዝግብ ተደጋጋሚ ግጭቶች በሚከሰቱባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት ነግሷል። መስከረም 18 ቀን በርካታ የጉራጌ ተወላጆች በቀቤና ልዩ ወረዳ የልዩ ወረዳ ምስረታ ጋር በተያያዘ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ 12-18 መስከረም 2016ን ይመልከቱ)። በተጨማሪም በመስከረም አጋማሽ ላይ በመስቃን ወረዳ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች በማረቆ እና በመስቃን ብሔረሰቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ተከስቶ ነበር (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ 19-25 መስከረም 2016ን ይመልከቱ)።
በመጨረሻም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለአምስት ወራት አቋርጦት የነበረውን የምግብ ዕርዳታ ስርጭት መስከረም 29 ቀን መጀመሩን አስታውቋል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከዩኤስኤድ ጋር በሚያዚያ 2015 ወር እንዳስታወቀው “እርዳታ በአግባቡ ባለመሰራጨቱ” ምክንያት የምግብ ዕርዳታ ስርጭቱን እንደሚያቆም አስታውቆ ነበር።8ሮይተርስ፣ ‘የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ ማከፋፈሉን ቀጥሏል፣’ መስከረም 29, 2016 በሚያዝያ 2015 ወር የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ዩኤንኦሲኤችኤ) እንዳመለከተው “የምግብ ዕርዳታ በጣም ለተቸገሩት በብቃት እና በአግባቡ መድረሱ ከተረጋገጠ” የእርዳታ ስርጭቱ እንደሚቀጥል አመላክቶ ነበር።9ዩኤንኦሲኤችኤ፣ ‘ኢትዮጵያ የሁኔታዎች አዲስ መረጃ፣’ ግንቦት 4, 2015