የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
አማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን የኦሮሞ እና የአማራ ብሔር ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ተዋግተዋል። በኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ከመንግስት ኃይሎች ጋር በተለያዩ ቦታዎች ተዋግቷል። ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የተመዘገቡ የፖለቲካ ግጭቶች በመላ አገሪቱ ከ50% በላይ ቀንሰዋል።
ብሔር ተኮር ውጊያዎች በአማራ ክልል
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች በሰሜን ወሎ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች መከሰታቸው የተዘገበ ሲሆን ይኸም ባለፈው ሳምንት በክልሉ ያለው ግጭት በመጠኑ መቀነሱን ያሳያል። ከየካቲት ወር አጋማሽ ጀምሮ በክልሉ በፋኖ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረገው ውጊያ ወደ ከተሞች በመዛመቱን ተከትሎ በክልሉ ያለው ውጊያ ተባብሶ ነበር።
የፋኖ ታጣቂዎች እና የፌደራል መንግስትን ወደ ሰላም ድርድር ለማምጣት ያልተቋረጠ ጥረት እየተደረገ አይደለም። ሆኖም በመጋቢት 3 ቀን የኢትዮጵያ የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ መንግስት “ጥያቄ አለኝ ከሚል ቡድን ጋር ለመደራደር” ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።1ቦርከና፣ ‘የኢትዮጵያ መንግስት “ከየትኛውም ቡድን ጋር በማንኛውም ጥያቄ ለመደራደር ዝግጁ ነኝ አለ” መጋቢት 3, 2016 መንግስት ለድርድር መዘጋጀቱን የተገለጸ ቢሆንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቃዋሚ የምክር ቤት አባልና የመንግሥት ወጪና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩትን የክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ድምፅ ሰጥቷል።2ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሣ፣’ መጋቢት 5, 2016 ክርስቲያን ታደለ በአማራ ክልል ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ በነሐሴ 2015 በቁጥጥር ስር ውለዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጥር ወር ታሰረው የነበሩት ሌላው የተቃዋሚ የፓርላማ አባል ደሳለኝ ጫኔ መጋቢት 5 ቀን ከእስር ተፈትተዋል።3ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘ደሳለኝ ጫኔ ከእስር ተለቀቁ፣’ መጋቢት 5, 2016
ይህ በእንዲህ እንዳለ መጋቢት 1 እና 2 በኦሮሞ እና በአማራ ብሔር ታጣቂዎች መካከል ዳግም ውጊያ መቀስቀሱ የተዘገበ ሲሆን በሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ በተከሰተው ውጊያ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጂልዬ ጥሙጋ ወረዳም በሁለቱ ታጣቂዎች መካከል ከመጋቢት 1 እስከ 3 ቀን ደረስ የሰው ህይወት የቀጠፈ ውጊያ ተደርጓል። በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ያለው ግጭት አልፎ አልፎ የሚቀሰቀሰ — ከጊዜ በፊት ውጊያ የተቀሰቀሰው በታህሳስ ወር ነው — እና በሀገሪቱ ውስጥ በአማራ እና በኦሮሞ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ከፍተኛ ውጥረት ያመላክታል።
በኦሮሚያ ክልል ውጊያ እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት
በኦሮሚያ ክልልም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ቀጥሏል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉደቱ ቆንዶሌ ወረዳ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባቦ ወረዳ በቡድኑ ላይ ዘመቻ እየተደረገ እንደሆነ የመንግስት ምንጮች አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በአርሲ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ተጨማሪ ውጊያዎች መከሰታቸውም ተዘግቧል።
በተጨማሪም በአርሲ ዞን ከደራ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አምስት ሠራተኞች ከሁለት ሳምንት በፊት ታግተው ከተወሰዱ በኃላ ባለፈው ሳምንት ተገድለው ተገኝተዋል። በኦሮሚያ ክልል በውጊያዎች መስፋፋት ምክንያት እገታዎች ከባለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ ጨምረዋል።
መፈናቀል በትግራይ ክልል
መጋቢት 3 ቀን ከምዕራብ ትግራይ ዞን ከሁመራና አካባቢዋ መንደሮች የተፈናቀሉ ተጨማሪ 28 የትግራይ ተወላጆች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን በምትገኘው ሽሬ ከተማ ደርሰዋል።4ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ዮሃንስ ገብረ-እግዚአብሄር፣ ‘ትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች እሮሮ፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ መጋቢት 4, 2016 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ከጥቅምት 2013 ጀምሮ የአማራ ኃይሎች የምዕራብ ትግራይ ዞን ተቆጣጥረውታል። በ2013 ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከተፈናቀሉት በሺዎች ከሚቆጠሩት ሰዎች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቁጥር ያለው ቢሆንም ከእነዚህ የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉት የትግራይ ተወላጆች ጉዳይ ጉልህ ነው (የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከጥር 23 እስከ የካቲት 21, 2016ን ይመልከቱ)።
መጋቢት 2 ቀን የትግራይ ጊዜያዊ ክልላዊ አስተዳደር እና የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር በአፍሪካ ህብረት በመታገዝ በኢትዮጵያ የዘለቂ የጦርነት ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።5የአፍሪካ ህብረት፣ ‘የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የተከበሩ ሙሳ ፋኪ ማሃማት የጦርነት ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ላይ በ1ኛው ስልታዊ ነጸብራቅ ወቅት ላይ የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 2, 2016 ይህ ስምምነት በጥቅምት 2015 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን አስከፊ ግጭት ለማስቆም በትህነግ/ህወሓት እና በመንግስት ተፈርሟል። የአውሮፓ ህብረት እና የቡድን 7 ሀገራት በመጋቢት 4 ቀን መግለጫ አውጥተው ስብሰባውን በአሉታዊ ተቀብለው የተፋላሚዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እና አደረጃጀታቸውን ለማፍረስ እንዲሁም በግጭቱ የተጎዱ ወገኖችን ችግር ለመፍታት ተጨማሪ መሻሻል እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።6የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ፣ ‘የጋራ መግለጫ፣’ መጋቢት 4, 2016