የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ክልል ውጊያዎች የተመዘገቡ ሲሆን በዚህም የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል። በሌላ ቦታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በምዕራብ ኦሮሚያ የምትገኝ ቁልፍ ከተማን የጎበኙ ሲሆን በጋምቤላ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል።
በአማራ ክልል በፋኖ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሰላማዊ ሰዎች ተጎዱ
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መደረጉ ተዘግቧል። በሰሜን ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ ወደ ወልዲያ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች በመንገድ ዳር በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ ቆስለዋል።1ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በግጭት መሀል በሚጓዙ የሰሜን ወሎ ዞን መንገደኞች መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፣’ ግንቦት 3, 2016 ይህ መንገድ – A2 መንገድ – ከየካቲት እስከ ሚያዝያ መጀመሪያ ድረስ በፀጥታ ችግር ምክንያት በፀጥታ ኃይሎች ተዘግቶ ነበር።
ከሚያዚያ 2015 ጀምሮ በመላው አማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ሲካሄድ ቆይቷል (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015 እና የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከ25 ሐምሌ እስከ 25 ነሐሴ 2015ን ይመልከቱ)። ግንቦት 3 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአማራ ክልል የታጠቁ ኃይሎችን ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጠይቀዋል።2የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህር ዳር ከተማ አዲሱ የዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ያደረጉት ንግግር፣’ ግንቦት 4, 2016 በሚያዝያ ወር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የታጠቁ ቡድኖች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ በመጠየቅ ለተሳታፊ ተወካዮች የጥበቃ ዋስትና እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።3ሸዋንግዛው ወጋየሁ እና እሸቴ በቀለ፣ ‘የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጥሪ፣’ ሚያዝያ 12, 2016 ባለፈው ሳምንት የጎጃም የፋኖ ተወካይ በይፋ እንዳልተጋበዘ እና መንግስት በኮሚሽኑ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ስላለው እንደማይሳተፍ ጠቁመዋል።4ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ፣’ ሚያዚያ 30, 2016 የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግስት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እየተባለ የሚጠራው — በተመሳሳይ መልኩ በይፋ እንዳልተጋበዘ እና እንደማይሳተፍም አመልክቷል። ኮሚሽኑ የታጠቁ ቡድኖችን ለማግኘት መቸገሩን በመጥቀስ ይፋዊ ግብዣ እንዳልላከ አምኗል።5ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ፣’ ሚያዚያ 30, 2016
አብይ ነቀምቴን ጎበኙ
ሚያዚያ 30 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተዋል። ህዝቡን ባነጋገሩበት ወቅት ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ አካባቢው በፀጥታ ችግር ምክንያት በልማት ወደ ኋላ የቀረ መሆኑን ጠቅሰዋል።6ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘“ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፤ ትናንትና ታግለን በደማችን አሸንፈናል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወለጋ፣’ ሚያዚያ 30, 2016
በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ፀረ-መንግስት እንቅስቃሴ የተነሳ ሰፊ የፀጥታ ችግር ቢከሰትም የኦሮሚያ ክልል አሁንም የመንግስት ደጋፊዎች መሰረት ነው። አብይ የጠቅላይ ሚንስትርነታቸውን ሰባተኛ አመት ሲጀምሩ ይህን እድጋፍ መሰረት ለማስፋት እና በኦሮሚያ — በትውልድ ክልላቸው7አብይ አህመድ የተወለዱት በኦሮሚያ በጅማ ዞን በሻሻ ከተማ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ነበሩ። — እንደ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ያሉ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች በብዛት በሚገኙበት የምዕራብ ኦሮሚያን ጨምሮ ድጋፉቸውን ለማጠናከር ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ላይ ያነጣጠረ የመንግስት ዘመቻ ጋር የተያያዙ ውጊያዎ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ሪፖርት እየተደረጉ ይገኛሉ። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በምስራቅ ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች በታጣቂ ቡድኑ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መደረጉን የመንግስት ምንጮች ጠቁመዋል።
በጋምቤላ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጥቃት
በጋምቤላ ክልል ሚያዚያ 27 ቀን በጋምቤላ ዙሪያ ወረዳ አቦል ከተማ አቅራቢያ የህዝብ አውቶቢስ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ያደረሱ ሲሆን አውቶቢሱን ሲያጅቡ የነበሩ የክልሉ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል። አውቶቢሱ ከኢታንግ ልዩ ወረዳ ወደ ጋምቤላ ከተማ በመጓዝ ላይ ነበር። ከዚይ ቀደም የጋምቤላ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ከሰፈነባቸው አካባቢዎች አንዱ ነበር። ይሁን እንጂ በአካባቢ ግጭጥ እና ከደቡብ ሱዳን የድንበር ዘለል ጥቃት ጋር በተያያዘ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ግጭት እየጨመረ መጥቷል።
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሚያዚያ 26-ግንቦት 2, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከሚያዚያ 26 እሰከ ግንቦት 2, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 19 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 3 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 0 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት