በዚህ ከጥር 17 አስከ የካቲት 7, 2017 ያለውን ሁኔታ በሚሸፍን ዘገባ

በኦሮሚያ በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ያለው ውጊያ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ቢሆንም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ግን ቀጥሏል
በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በሸኚ ነጋሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግስት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ቡድን መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ቁጥር በኦሮሚያ ክልል በ60% ቀንሷል። ውጊያው የቀነሰው የዚህ አንጃው ኃይሎች ወደ ተሃድሶ ካምፖች መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው (ለተጨማሪ መረጃ ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ታኅሣሥ 1, 2017) እና ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ታኅሣሥ 8, 2017) ይመልከቱ)። ከጥር 17 እስከ የካቲት 7 አክሌድ አንድ ውጊያ ብቻ የመዘገበ ሲሆን ይኸውም በየካቲት 12 ቀን በሸገር ከተማ ሱሉልታ ወረዳ ሞዬ ጋጆ በተባለ ቦታ ኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ በመንግስት ኃላፊዎች እና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ያደረገውን የደፈጣ ጥቃት ተከትሎ የተመዘገበ ነው። ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ፣ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊን እና በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን የገደሉ ሲሆን ታጣቂዎቹ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የፀጥታ ኃይሎችን ከሱሉልታ ወረዳ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ጋር አፍነው ወስደዋል። ከህዳር ወር አጋማሽ ጅምሮ በመንግስት ኃላፊዎች ላይ የሚደርሰው የጥቃት መጠን እየጨመረ የመጣ ሲሆን አብዛኞቹ ጥቃቶች በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈፀሙ ናቸው ።
መንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ወታደራዊ ዘመቻዎችን ከሌሎች ስልቶች ጋር በማጣመር የቡድኑን ተፅእኖ ለመቀነስ ሞክሯል። ጥር 25 ቀን የኢትዮጵያ እና የኬንያ መንግስታት የኮንትሮባንድ ንግድን እና የሰዎችን እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን የሚያካትት የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመግታት በማለም በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በሚገኘው የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ላይ የጋራ ዘመቻ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።1የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘ኢትዮጵያ እና ኬንያ በኦነግ/ሸኔ ላይ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ጀመሩ፣’ ጥር 25, 2017 ኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ የኢትዮጵያ መንግስት የኬንያ ባለስልጣናትን እያሳሳተ ነው በማለት ዘመቻውን በመተቸት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችን በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል ሲል ከሰዋል።2አብረሃም ተክሌ፣ ‘ኢትዮጵያ እና ኬንያ በኦነሠ መደበቂያ ቦታዎች ላይ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት ጀመሩ፣’ ሪፖርተር፣ የካቲት 1, 2017 አብይ በ2012 በድንበር ላይ የሚገኙትን የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ታጣቂዎችን ለመከላከል የኬንያን እርዳታ ከጠየቀ ጀምሮ ሁለቱ መንግስታት የቀጠናዊውን ፀጥታ ለማጠናከር በሚደረገው የትብብር እርምጃዎች ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል።3ሳዲቅ ከድር አብዱ፣ ‘የኢትዮጵያና የኬንያ የስለላ ኃላፊዎች ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተወያዩ፣’ አናዶሉ ኤጀንሲ፣ ነሐሴ 16, 2016
ምንም እንኳን ኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ የሚሳተፍባቸው ግጭቶች በክልሉ እየቀነሱ ቢገኝም የፖለቲካ ግጭች በተለይም የመንግስት ኃይሎችን ጨምሮ በተለያዩ ቡድኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አሁንም ቀጥለዋል። ከጥር 17 እስከ የካቲት 7 አክሌድ በክልሉ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ስድስት ጥቃቶችን የመዘገበ ሲሆን 15 ሰዎች በእነዚህ ጥቃቶች ተገለዋል። በጅማ ዞን በጌራ ወረዳ በዋላ ቀበሌ የካቲት 6 ቀን በትንሹ ወደ 10 የሚጠጉ ታጣቂዎች አንድ ታዋቂ የቡና ባለሀብትን መግደላቸውን ተከትሎ በጅማ እና በጭራ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ የተደረጉ ሲሆን መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንዲያስቆም ጠይቀዋል። ባለሀብቱ በቅርቡ ወደ 200 የሚጠጉ የአርሶ አደሮችን መሬቶችን ለኢንቨስትመንት ተቀብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በኢንቨስትመንቱ በተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ መፍጠሩ የተነገረ ሲሆን አንዳንዶቹ ባለሀብቱ ላይ ማስፈራሪያ ዛቻ አድርገው እንደነበር ተዘግቧል።4 ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘በጅማ ዞን የአንድ ባለሀብት ግድያን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለው ክስተት፣’ የካቲት 10, 2017፤ ሥዩም ጌቱ፣ ሸዋዬ ለገሠ እና ኂሩት መለሰ፣ ‘በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ሰዎችን ያፈናቀለው ግጭት፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 11, 2017
የታጣቂው ቡድን ማንነት ባይታወቅም አንዳንዶች የአማራ ተወላጆች ባለሀብቱን ገድለዋል ብለው ከሰዋል።5ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘በጅማ ዞን የአንድ ባለሀብት ግድያን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለው ክስተት፣’ የካቲት 10, 2017 በመሆኑም የባለሃብቱ ግድያ በወረዳው ውስጥ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የአጸፋ ጥቃቶችን አስከትሏል። በቦሬ ከተማ እና ኦባ ቀበሌ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የኦሮሞ ወጣቶች — በአካባቢው ቄሮ በመባል የሚታወቁ — የአማራ ተወላጆችን እና ንብረቶቻቸውን ማጥቃታቸውን ተከትሎ በትንሹ 10 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። ከ7,000 በላይ ሰዎች — አብዛኛው የአማራ ተወላጆች የሆኑ — ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልል ተሰደዋል።6ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘በጅማ ዞን የአንድ ባለሀብት ግድያን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለው ክስተት፣’ የካቲት 10, 2017 የክልሉ ፖሊስ በባለሃብቱ ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለፀ ሲሆን፥ የክልሉ መንግስት ድርጊቱን የኃይማኖትና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው ሲል ለጊዜው ያልታወቁ አካላት ከሷል።7ስቡክ @ኦሮሚያቢሲ፣ የካቲት 9, 2017
በአማራ ሰላማዊ ሰዎች በጤና፣ በትራንስፖርት እና በትምህርት አገልግሎት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ይደርስባቸዋል
በአማራ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመሰረታዊ አገልግሎቶች እና የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከጥር 17 እስከ የካቲት 7 አክሌድ ስድስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የመዘገበ ሲሆን ሰባት ሰዎች በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት መገደላቸው ተዘግቧል። ጥር 24 ቀን በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ዳይሬክተር እና የቀዶ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ በዋና ከተማዋ ባህርዳር ከተማ ከስራ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመተው ተገድለዋል። የዚሁ ሆስፒታል ሌላ ሀኪም ግድያው ከመከሰቱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተመሳሳይ አጥቂዎች በጥይት ተተኩሶባቸው መትረፋቸው ተነግሯል። ይህ ግድያ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች በፀጥታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንዲደረግ እና በሆስፒታሉ ሠራተኞች ተቃውሞ እንዲያደርጉ የገፈፋ ሲሆን መንግስት የጤና ባለሙያዎችን ደህንነት እንዲያረጋግጥ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ጠይቀዋል። የጤና ሠራተኞች የፋኖ ግጭት ከጀመረበት ከመጋቢት 2015 መጨረሻ ጀምሮ የተለያዩ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል። ከመጋቢት 23, 2015 እስከ የካቲት 7, 2017 ድረስ አክሌድ በጤና ባለሙያዎች እና ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ 18 የግጭት ኩነቶችን ከአምስት የአየር ድብደባዎች ጋር ጨምሮ መዝግቧል።
በአማራ በመንገዶች ላይ የሚደርሰው ጥቃትም በነዋሪዎችና በተጓዦች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። ጥር 25 ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ናረው ዳረጋ ቀበሌ አወዳዳ ጎጥ የተባለ አካባቢ ወደ ስምንት ከሚጠጉ ታጣቂዎች ሚኒባስ በማስቆም 13 ተሳፋሪዎችን አፍነው እየወሰዱ በነበረበት ወቅት ከአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተዋግተዋል። ከውጊያው በኃላ ያታፈኑት ሰዎች ተለቀዋል። ጥር 29 ቀን በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደውሃ ከተማ አቅራቢያ ሶስት ታጣቂዎች አንድ ሰው ተኩሰው ሲገድሉ አራት ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ማቁሰላቸው ተነግሯል። ታጣቂዎቱ ከገንደውሃ ከተማ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረውን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በማስቆም ተሳፋሪዎችን የዘርፉ ሲሆን ዝርፍያውን የተቃወሙት ላይ ተኩሰ ከፍተዋል።
የፋኖ ግጭት መጋቢት 2015 መጨረሻ ላይ ከጀመረ በኃላ በትራንስፖርት አገልግሉት ላይ ያነጣጠረ አፈና እና ዝርፊያ መስፋፋት የጀመረ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በምዕራብ አማራ የሚገኘው ጎንደር–መተማ መስመር ያሉ የተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎች መስጠት አቁመዋል ወይም ጥቃት በመሸሽ ረጅም መንገዶችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም ተሽከርካሪዎች በመንግስት ኃይሎችም ሆነ በፋኖ ታጣቂዎች በተቋቋሙ የተለያዩ ኬላዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በመገደዳቸው የመሰረታዊ እቃዎች ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።8አበበ ፍቅር፣ ‘በአማራ ክልል የአሽከርካሪዎች ዕገታን መደበኛ የሥራ ቦታ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው መበራከቱ ተገለጸ፣’ ሪፖርተር፣ የካቲት 9, 2017
አፈና እና ጥቃትም በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ይገናል። ለአብነትም የካቲት 5 ቀን ፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ጎጃም ዞን ቆሬ ጠንከረ ቀበሌ በሚገኘው ቆሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 13 መምህራንን በማፈን መምህራኑን ለመልቀቅ እስከ 50,000 የኢትዮጵያ ብር ቤዛ ጠይቀዋል። መንግስት ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው እንዲቀጥሉ ትእዛዝ ቢሰጥም የፋኖ ታጣቂዎች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን ትእዛዛቸውን የማይፈጽሙ መምህራን በተደጋጋሚ አፍነው ወስደዋል። የያዝነው የትምህርት ዘመን ከጀመረበት መስከረም 2017 ጀምሮ አክሌድ በአማራ ክልል መምህራን ላይ ያነጣጠሩ አራት ጥቃቶችን መዝግቧል።