በሰሜን የሚገኘው የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር እንዲሁም ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያ፣ አፋር እና ከትግራይ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። ከቅርብ አመታት ወዲህ ክልሉ  የተለያዩ አይነት ግጭቶችን አስተናግዷል። ከሰኔ 2013 ጀምሮ የትግራይ ግጭት ወደዚህ ክልል የተስፋፋ ሲሆን ከአብዛኛዎቹ አጎራባች ክልሎች እና ሱዳን ጋርም ከድንበር ጋር የተያያዙ ውዝግቦች አሉ። በተጨማሪም በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች አናሳ ብሄረሰቦች አምፀው ከመንግስት ሃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። ይህ ክፍል በዚህ ክልል ላይ የተሰሩ ዘገባዎችን ያካትታል።