በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 25, 2014-ሰኔ 2, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,102
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 5,683
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,586
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 26-ሰኔ 2, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 10
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 15
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 15
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች ሰልፎች ሲካሄዱ ጦርነቶች እንዲሁም በሰላማዊ ሰዎች እና በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ጨምሮ የፖለቲካ ጥቃቶች በኦሮሚያ ክልል ቀጥለዋል።
በትግራይ ክልል ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ግንቦት 27 ቀን ክርክር ባለበት የምዕራብ ትግራይ ዞን የአማራ ተወላጆች በማይካድራ፣ ሁመራ፣ ዳንሻ፣ ፀገዴ፣ ቆራሪት፣ ማክሰኞ ገበያ፣ ወፍ አርግፍ፣ ቤተመሉ፣ በአከር እና ወልቃይት ከተሞች ሰልፍ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ በዞኑ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሁኔታን አስመልክቶ መንግስት መፍትሔ እንዲሰጥ እና በአካባቢው ላሉ ከተሞች በመንግስት የተመደበውን በጀት እንዲለቅ ጠይቀዋል። በአዲ ረመጽም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተካሂዷል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚካሄድ ተቃውሞ ከአማራ ክልል በመጡት የአስተዳደር አካላት የሚበረታታ ነው። በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት፣ ሁመራ እና ፀገዴ በአሁኑ ወቅት በ2013 የሰሜኑ ግጭት ሲጀመር አካባቢውን በኃይል በተቆጣጠሩት ከአማራ ክልል በመጡ ባለስልጣናት ይፈ ባልሆነ መልኩ የሚተደደር ነው። አካባቢው የተለያዩ ብሔሮች አብረው የሚኖሩበት ቢሆንም አካባቢው ከ1984 እስከ 2012 ድረስ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) በትግራይ ስር ይመራ ነበር። ልክ እንዳለፈው ሳምንት በዚያን ጊዜም በአከባቢው የሚኖሩ አማራዎች ከአማራ ክልል ጋር ለመቀላቀል በመፈለግ ተመሳሳይ የሆኑ ተቃውሞዎችን በተደጋጋሚ ያደርጉ ነበር። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተመሳሳይ ተቃውሞዎችን ያወገዘ ሲሆን የክልሉን የግዛት አንድነት ማስጠበቅ የጊዚያዊ መንግስቱ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጿል2ዋዜማ ሬዲዮ፣ ‘ለቸኮለ! ዓርብ መጋቢት 15/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች፣’ መጋቢት 15, 2015፤ ቦርከና፣ ‘ራያ የማንነት ጥያቄውን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግስት ህጋዊ ምላሽ ጠየቀ፣’ መጋቢት 10, 2015 (ክርከር ስላለበት የምዕራብ ትግራይ ዞን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦን የትግራይ ጦርነት ገጽ ይመልከቱ)።
እንዲሁም ግንቦት 28 ቀን የትህነግ/ህወሓት የቀድሞ ታጋዮች – በአብዛኛው ወጣት ወንዶች – በክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እና የምግብ አቅርቦት እጦት በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል። ከሁለት ቀናት በኋላ በመቀሌ የሚገኙ ጡረተኞች በግጭቱ ወቅት የትግራይ በጀት በመቋረጡ ምክንያት ክፍያ ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የጡረታ ጥቅማጥቅም እንዲከፈላቸው በመጠየቅ ሰልፍ አድርገዋል።
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ስር በነበሩበት ወቅት ያገኙት የነበረውን የመንግስትን አገልግሎት መንግስት በአዲስ መልክ በተመሰረተው የምስራቅ ቦረና ዞን ስር ካካተታቸው በኃላ በተገቢው መንገድ አለማግኘታቸውን በመቃወም ግንቦት 29 ቀን በሻኪሶ ከተማ ስልፍ ተደርጎ ነበር። በማግስቱም የተቃውሞ ሰልፍ የቀጠለ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች ሰልፈኞችን ለማስቆም ጣልቃ በመግባታቸው ቢያንስ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል። የነገሌ ቦረና ከተማን በምስራቅ ቦረና ዞን ስር ለማካተት መንግስት መወሰኑን በመቃወም በዋደራ ከተማም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተካሂዷል። በየካቲት ወር የሰው ህይወት ህልፈት ያስከተሉ ፖሊስ ሊያስቆማቸው የሞከረው በርካታ የተቃውሞ ኩነቶች በቀድሞው የጉጂ ዞን ተመዝግበው ነበር (መንግስት ዞኑን መልሶ ለማዋቀር ሰለወሰነው ውሳኔ እና ውሳኔውን በመቃወም ስለተደረጉ ሰልፎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 18–24, 2015 ይመልከቱ)።
በተጨማሪም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ – የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት – በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ አቅራቢያ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ ጥቃት ያደረሰ ሲሆን በዚህም ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ደግሞ ቆስለዋል። ብዙም ሳይቆይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ በመግባት ከቡድኑ ጋር ተዋግቷል። ሰኔ 1 እና 2 በሆሮ ጉዱሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በአገምሳ ከተማ በአንዳንድ የአካባቢው ምንጮች ፋኖ በመባል የሚታወቁት የአማራ ብሔር ታጣቂዎች ቢያንስ ሶስት ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። እንዲሁም ሰኔ 1 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን በበካት ከተማ የአዳ በርጋ ወረዳ ምክትል ኃላፊን በመኖሪያ ቤታቸው ተኩሰው ገድለዋል። በማግስቱ ታጣቂዎች በምዕራብ ወለጋ ዞን በላሎ አሳቢ ወረዳ ኢናንጎ አካባቢ በአምቡላንስ ላይ ተኩስ ከፍተው ከአዲስ አበባ በመመለስ ላይ በነበረ አንድ የጤና ባለሙያ እና የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት አባልን ገድለዋል።
በመጨረሻም ከኦነግ-ሸኔ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለሦስት አመታት ያህል ተዘግቶ የነበረውን የጋምቤላ-ደምቢ ዶሎ መንገድን ለመክፈት ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ኦፕሬሽን አካሂደዋል።3ጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት፣ ‘ለሶስት አመታት በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ከጋምቤላ ወደ ሸበል ደንቢዶሎ የሚወስደው መንገድ ለማህበረሰቡ ክፍት መሆኑ ተገለፀ፣’ ግንቦት 26, 2015 በታንዛኒያ የተካሄደው አጭር የሰላም ንግግር “በዚህ የውይይት ዙር አንዳንድ ጉዳዮች” ላይ ስምምነት ባለመኖሩ ምክንያት ያለምንም ስምምነት ካበቃ በኃላ በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ያለው ግጭት በግንቦት ወር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።4ጁሊያ ፓራቪሲኒ፣ ‘በኢትዮጵያ እና በኦሮሞ አማፂዎች መካከል የተደረገው የመጀመሪያው ዙር የሰላም ድርድር ያለምንም ስምምነት አበቃ’ ሮይተርስ፣ ሚያዚያ 25, 2015 በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በመበተኑ መንግስት ኦነግ-ሼኔን ለመዋጋት በሚያደረገው ጥረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወት አድርጓታል። የዚህ መንገድ መከፈት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሀገሪቱ ውስጥ ወሳኝ ቦታዎችን ለመያዝ የተሻለ አቅም ያለው ኃይል መሆኑን አመላካች ሊሆን ይችላል።