በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 17-23, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 26
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 124
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 28
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 18, 2015-ጥቅምት 23, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,186
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,744
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,371
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በኦሮሚያ ክልልም ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ተዘግበዋል።
የፋኖ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን እና አጣዬ ከተሞች፣ በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ እና በመርሳ ከተሞች ተዋግተዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በላሊበላ አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎችም አንዳንድ ውጊያዎች እና የመድፍ ተኩስ ተዘግበዋል።2ጉሊያ ፓራቪቺኒ እና ዳዊት እንዳሻው፣ ‘በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ግጭት በጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት ላይ ስጋት ፈጥሯል፣’ ጥቅምት 27, 2016 በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ለወራት እንደቀጠሉ ሲሆን እያስከተለ ያለው ሞትም እንደቀጠለ ነው። የውጊያው መራዘም በክልሉ የአስተዳደር ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። በአካባቢ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ ከሚፈፀመው ግድያ ባሻገር ባለፈው ሳምንት የወጣ ሪፖርት በብዙ አካባቢዎች ግብር መሰብሰብ እንዳልተቻለ ያመለክታል።3ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በግጭት ሳቢያ በቂ ግብር ባልተሰበሰበበት የአማራ ክልል ተጨማሪ ቀውስ አስግቷል፣’ ጥቅምት 20, 2016 በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ማስተማር አቁመዋል።4ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በአማራ ክልል ኹሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ፎረሙ ገለጸ፣’ ጥቅምት 23, 2016 ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የድሮን ጥቃት እና የቤት ለቤት ፍተሻን ጨምሮ በመንግስት በተከናወኑ ተግባራት ምክንያት የብዙ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ መፈፀሙን በማረጋገጥ ሪፖርት አውጥቷል።5የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ ‘አማራ ክልል: ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብዓዊ መብቶች እንድምታ፣’ ጥቅምት 19, 2016 ከሪፖርቱ መውጣት በኃላ መንግስት ባወጣው መግለጫ የኢሰመኮ ሪፖርት “በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ እና ሚዛናዊነት የሚጎድለው” መሆኑን በመጥቀስ ተችቶታል።6በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርት በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣’ ጥቅምት 22, 2016
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች መካከል በምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ወለጋ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግበዋል። በክልሉ ሰላማዊ ሰዎች የጥቃት ኢላማ መሆናቸው ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች አንድ በዕድሜ የገፉ ሴት እና ሌሎች ሶስት ወንዶችን ልጆቻችሁ የኦነግ-ሸኔ አባል ናቸው በማለት ካሰሩዋቸው በኃላ ጥይት በመተኮስ ሴቷን ጨምሮ ሶሰቱን መግደላቸው እና አንድ ሰው ማቁሰላቸው ተነግሯል። በሌላ በኩል የኦነግ-ሸኔ ኃይሎችም በሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ እና ደራ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ በማድረግ ባደረሱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን በመግደል እና በማፈናቀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
በደቡብ እትዮጵያ ህዝቦች ክልል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ፀብን ተከትሎ ፖሊስ አንድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አባል በሆነ ግለሰብ ላይ በፈፀመው ድብደባ ግለሰቡ ህይወቱ አልፏል። እንደ ኢዜማ ማግለጫ መሰረት የሟቹን ጉዳይ በመከታታል ላይ የነበሩ ሌሎች 28 የፓርቲው አባላትም የቀበሌ አጥር ደብድባቹኃል በሚል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ክስተቱን ተከትሎ ፓርቲው ባወጣ መግለጫ ድርጊቱን በፈፀሙ የፀጥታ አባላት ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እና ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች “የስነ ምግባር እና የሙያ ክህሎት ስልጠና አንዲሰጣቸው” ጠይቋል።7የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)፣ ‘በፓርቲያችን አባል ሕልፈት የተሠማንን ሐዘን እየገለፅን አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን!፣’ ጥቅምት 20, 2023 ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ በተጨማሪ የኢዜማ አባላት በተለያዩ የሀገሪቷ ቦታዎች የፖለቲካ ጥቃቶች ኢላማ ሆነዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ቢያንስ ሶስት የፓርቲው አባላት በታጣቂ ቡድኖች ተገድለዋል። በቅርቡ በ2013 በተደረገው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኢዜማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራት መቀመጫዎችን ያሸነፈ8የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ‘ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ድምፅ የተሰጠባቸው የተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች ላይ ፓርቲዎች ያገኟቸው መቀመጫዎችን የሚያሳይ ማጠቃለያ፣’ ሐምሌ 3, 2013 ሲሆን ሊቀመንበሩ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ምክንያት የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግስት የካቢኔ አባል ናቸው።
በትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ትሕነግ/ህወሓት) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ግጭቶችን በቋሚነት በማቆም ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በፕሪቶሪያ ስምምነት የተፈረመበት አንደኛ አመት ባለፈው ሳምንት የሞላ ሲሆን ስምምነቱም የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትን የቋጨ ነው። የፌዴራል መንግስት “ውዝግብ የተነሳባቸው” የትግራይ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚመለሱ መሆኑን እና የአካባቢዎቹ እጣ ፋንታም በህዝበ ውሳኔ የሚወሰን መሆኑን ጥቅምት 26 ቀን አስታውቋል።9የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ግጭቶችን በቋሚነት ለማቆም በፕሪቶሪያ የተደረሰ ስምምነትን አንደኛ አመት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተሰጠ መግለጫ፣’ ጥቅምት 26, 2016 ግጭቱ ጥቅምት 2013 ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የምዕራብ እና ደቡባዊ ትግራይ ዞኖች በግልጽ እውቅና ሳይሰጣቸው በአማራ ክልል ስር ራስ ገዝ አካባቢ ሆነው በመተዳደር ላይ ይገኛሉ። ለአማራ ክልል ነዋሪዎች ምዕራብ ትግራይ የብሔርተኞች የድጋፍ ማሰባሰቢያ የሆነ ሲሆን በዚህም ምክንያት መንግስት አካባቢዎቹን ለትሕነግ/ህወሓት ከመለሰ ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል በአማራ ክልል በስፋት ይነገራል (ተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ልዩ ዘገባ፡ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ ወደ ሰላም የሚደረግ ጉዞ ይመልከቱ)።