በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 24-30, 20161 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 49
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 60
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 10
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 25, 2015-ጥቅምት 30, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,220
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,800
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,131
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ተባብሰዋል። ይህ በአንዲህ እንዳለ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው የሰላም ንግግር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚደረጉ ግጭቶች እንዲቀንሱ አድርጓል።
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የተባባሱ ሲሆን በማዕከላዊ ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ፣ በምዕራብ ጎጃም፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ወሎ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ግጭቶች ተከስተዋል(ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፋኖ ታጣቂዎችን ኢላማ በማድረግ የተፈጸመ የአየር ጥቃት በአንኮበር ወረዳ ውስጥ የሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት በመምታቱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። የፋኖ ታጣቂዎች ለአጭር ጊዜ የላሊበላ ከተማን መቆጣጠር የቻሉ ቢሆንም ጥቅምት 28 ቀን በተደረገ ውጊያ ከተማውን ለቀው ወጥተዋል። በ11ኛው ክፍለ ዘመን ከፍልፍል ድንጋይ በተሰራው እና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በአለም ቅርስነት በተመዘገበው ቤተ-ክርስትያን አቅራቢያ የሚደረጉ ውጊያዎች እና የከባድ መሳሪያ ጥቃቶች የቤተ-ክርስትያኑ ደህንነት ላይ ስጋት ፈጥረዋል።2አልጀዚራ፣ ‘የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦርቶዶክስ ቅድስት ቦታ ከሆነችው ከላሊበላ ከተማ ታጣቂ ቡድንን አስወጡ፣’ ጥቅምት 29, 2016 በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ለወራት የቀጠሉ ሲሆን እየጨመሩም ይገኛሉ።
በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ልዩ ዞን አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች በአማራ እና በኦሮሞ ብሔር ታጣቂዎች መካከል ውጊያዎች የተቀሰቀሱ ሲሆን ቢያንስ 18 ሰዎች ተገድለዋል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞን ድንበር አቅራቢያ በኦሮሞ እና በአማራ ማህበረሰቦች መካከል በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰታሉ (ተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ የኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ግጭት ገጽን ይመልከቱ)።
በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው) እና በፌዴራል መንግስት ተወካዮች መካከል ሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር በታንዛንያ እየተካሄደ መሆኑን ምንጮች ጥቅምት 27 ቀን ይፋ አድርገዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባን እና በኃላ ላይ ንግግሩን የተቀላቀሉት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን እና የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስተር ዶ/ር ጌዲዮን ጤሞቴዎስን ጨምሮ ከሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።3አዲስ እስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት ለማስቆም ሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር በዳሪ ሰላም ተጀመረ፤ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አዛዥ ተገኝተዋል፣’ ጥቅምት 28, 2016; አዲስ እስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር እየተካሄደ ያለው የሠላም ንግግረ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ በመሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በዳሪ ሰላም የሚገኙ የወታደራዊ አመራሮችን ተቀላቀሉ፣’ ኅዳር 3, 2016 ከዚህ በፊት የተደረገው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ንግግር በሚያዝያ 2015 ያለ ስምምነት ተጠናቋል (ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23, 2015 ወርሀዊ፡ የሰላም ንግግር ቢሞከርም በኦሮሚያ ዳግም ግጭት ተቀስቅሷል ይመልከቱ)። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፓርቲ እ.ኤ.አ 2019 ከተገነጠለ ጊዜ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔን ያሳተፈ ውጊያ የቀጠለ ሲሆን በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 1.4 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ተፈናቅሏል።4ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንደ ካፓሲቲ ቢዩልድንግ (ሲዲሲቢ)፣ ‘በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት ማስቆም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ የፖሊሲ ማብራርያ፣’ ጥቅምት 6, 2016
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ግጭት ቀጥሏል። ጥቅምት 30 ቀን ማንነታቸው ያልታወቀ ወጣቶች የአበሩስ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም 30 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ድርጊቱ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ጣልቃ በመግባቱ ሊቆም ችሏል። በጉራጌ ዞን በተለይም በወልቂጤ ከተማ ያለው ግጭት ከጥቅምት ጀምሮ እንደቀጠለ ነው። በቅርቡ የተመሠረተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞንን ለሦስት የአስተዳደር መዋቅሮች የከፈለ ሲሆን የምስራቅ ጉራጌ ወረዳን ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ሲወስን የቀቤና እና የማረቆ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው ‘ልዩ’ ወረዳ ሆነው እንዲዋቀሩ ተደርጓል።5ዋዜማ ራዲዮ፣ ‘የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕልውና በይፋ አከተመ፣’ ነሐሴ 13, 2015 ከዚህ ውሳኔ ጊዜ ጀምሮ ከዚህ በፊት በወሰን ላይ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ምክንያት በተደጋጋሚ ገጭቶች በሚከሰቱባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።
በትግራይ ክልል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በትግራይ ሕዝብ ነጸነት ግንባር (ትሕነግ/ሕወሓት) መካከል ከተፈጠረው ውዝግብ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት ሁለት የዞን አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ አራት ተጨማሪ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።6አዲስ እስታንዳርድ፣ ‘የፖለቲካ ዜና፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጨማሪ አራት ከፍተኛ ባለስልጣናትን አባረረ፣’ ጥቅምት 28, 2016 አራቱም ባለስልጣናት የትሕነግ/ሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።7ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በትግራይ አራት አመራሮች ከሓላፊነት የተነሡት “ሥራን ለመፈጸም ባለመቻል” እንደኾነ ክልሉ ገለጸ፣’ ጥቅምት 28, 2016 ይህ ውሳኔ ከሁለት ሳምንታት በፊት ሌሎች ስድስት አስተዳዳሪዎች ከስልጣን የተባረሩበትን እርምጃ ተከትሎ የመጣ ነው (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡10-16 ጥቅምት 2016ን ይመልከቱ)።