በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኅዳር 8-14, 20161 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 34
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 89
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 18
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኅዳር 9, 2015 -ኅዳር 14, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,236
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,792
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,309
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የሰላም ንግግር መክሸፉን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ግጭቶች የጨመሩ ሲሆን በአማራ ክልልም ውጊያዎች ቀጥለዋል።
በፌዴራል መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው) መካከል ሲካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ከስምምነት ሳይደርሱ ኅዳር 11 ቀን ተጠናቋል። መንግስት የሰላም ንግግሩን አለመሳካት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ አመራር “ለሰጥቶ መቀበል ዝግጁ አለመሆን” ጋር አያይዟል።2ሬድዋን ሁሴን፣ የትዊተር መልዕክት፣ ኅዳር 11, 2016፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘ከሸኔ ጋር በሁለት ዙር የተደረገው ንግግር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ፣’ ኅዳር 11, 2016 በምላሹ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ አመራር “የቀረበለትን ሰልጣን” አለመቀበሉን እና የመንግስት ተወካዮች “ለአገሪቱ መሠረታዊ የፖለቲካ እና የደህንነት ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት አላሳዩም” በማለት ወቅሷል።3ኦዳ ተርቢ፣ የትዊተር መልዕክት፣ ኅዳር 14, 2016 ይህ በሁለቱ ወገኖች መካከል ከጥቅምት የመጨረሻ ሳምንታት ጀምሮ በታንዛንያ ዳረ ሰላም የተካሄደ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር ነው። ከሚያዝያ 19-25, 2015 የተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ንግግር በተመሳሳይ ከስምምነት ሳይደረስ ተጠናቋል። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ አንጋፋ ፖለቲከኞች፣ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት እና ማህበረሰቡ የሰላም ንግግሩ ያለስኬት በመጠናቀቁ ቅር መሰኘታቸውን የገለፁ ሲሆን አንዳንዶቹ የሰላም ንግግሩ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት በመንግስት የተወሰዱ ወታደራዊ አርምጃዎችን አውግዘዋል።4ታዬ ደንደኣ አረዶ፣ የፌስቡክ መልዕክት፣ ኅዳር 11, 2016፤ ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የመብቶች ተሟጋች ተቋማት የታንዛኒያው ድርድር “ያለስምምነት የመጠናቀቁ መዘዝ አሳስቦናል” አሉ፣’ ኅዳር 13, 2016፤ ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የፓርላማ አባላቱ የታንዛኒያው ድርድር ሒደት ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጽ ጠየቁ፣’ ኅዳር 14, 2016፤ ሥዩም ጌቱ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር፣ ‘ያልሰመረው የመንግስት እና የኦነግ-ኦነስ ድርድር፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ ኅዳር 12, 2016
የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር በጀመረበት ሳምንት ማለትም ከጥቅምት 24-30 ባለው ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ የተሳተፈባቸው የፖለቲካ ግጭቶች ከዚያ በፊት ከነበሩ ሳምንታት ጋር ሲነፃፀር በ80% ቀንሰው ነበር። ሆኖም ግን የሰላም ንግግሩ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ በክልሉ ግጭቶች መጨመር የጀመሩ ሲሆን ከኀዳር 1 ቀን ጀምሮ ውጊያዎች አንደገና ጀምረዋል። ባለፈው ሳምንት በክልሉ ከሚገኙ 20 ዞኖች መካካል በ11ዱ ውስጥ 19 ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በዚህም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦነግ-ሸኔ መካከል በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በቡኖ በደሌ፣ በቦረና እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግቧል። ኅዳር 13 ቀን በቡኖ በደሌ ዞን መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ ኃይሎችን ኢላማ በማድረግ የአየር ጥቃት የፈፀመ መሆኑን የተነገረ ሲሆን ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች አና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደ ቀጠሉ ሲሆን በምስራቅ ጎጃም እና በሰሜን ወሎ ዞኖች ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግቧል። የፋኖ ታጣቂዎች ኅዳር 13 ቀን ከመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመዋጋት በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚገኘውን የማረሚያ ቤት ተቆጣጥረዋል። የፋኖ ታጣቂዎች የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ 600 ታራሚዎችን ካስለቀቁ በኃላ ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል። ምንም እንኳን አብዛኛውን የአማራ ክልል አካባቢዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር ቢሆኑም በወልዲያ የተፈፀመው አይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት በአብዛኛው የተበታተኑ የፋኖ ታጣቂዎች አቅማቸው እየጨመረ ስለመምጣቱ ሊያሳይ ይችላል (በአማራ ክልል ስላለው ግጭት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ: ከሐምሌ 25 አስከ ነሐሴ 25, 2015ን ይመልከቱ)።
በመጨረሻም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ሰዎች በተማሪዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት አንድ ሰው ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቷል። በምስክሮች መሠረት ጥቃቱ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው።5ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በወልቂጤ ከተማ ማንነትን የለየ ጥቃት እንደቀጠለ መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ፣’ ኅዳር 12, 2016 ይህ ጥቃት ከጥቅምት 21 እስከ ኅዳር 20, 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ በተማሪዎች ላይ የተፈፀመ ሁለተኛው ጥቃት ነው (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጥቅምት 24-30, 2016ን ይመልከቱ)። በወልቂጤ ከተማ እና በአቅራቢያው በሚገኘው የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር እና በአስተዳደሩ ውስጥ ሊኖር ከሚገባው የብሔሮች ውክልና ጋር በተያያዘ አልፎ አልፎ ግጭቶች እየተከሰቱ ሲሆን ከተማዋ በአሁኑ ጊዜ በፌዴራል ኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር ትገኛለች (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ መስከረም 26-ጥቅምት 2, 2015ን ይመልከቱ)።