በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሰኔ 25, 2013)1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,628
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 8,319
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,434
በቁጥር (ከሰኔ 19, 2013 እስከ ሰኔ 25, 2013)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ። በተለይም በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ጥቃት በተመለከተ ዘገባዎች ቀስ ብለው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊወጡ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 8
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 141
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 41
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ወደ ማዕከላዊ ትግራይ የከፈተውን ከባድ ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ የፌደራል ሃይሎች እና የኤርትራ አጋሮቻቸው ሰኔ 21, 2013 ላይ ክልሉን ለቀው ሲወጡ የሕወሓት ሃይሎች የክልሉ ዋና ከተማ የሆነውን መቀሌ ለመቆጣጠር ወደፊት ገፍተዋል። የሕወሓት እየገፉ ባለበት ወቅት የፌዴራል መንግሥት ብዙ ጊዜ ህዳር ወር አካባቢ ላይ የሚሆነውን “የግብርና ወቅት መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ” የአንድ ወገን ተኩስ አቁም መወሰኑን አስታውቋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 21, 2013)። የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮችን ከክልሉ እንዲያስወጣ የወሰነው በተለያዩ ምክንያቶች ሲሆን ከዚህ በታች ባለው ሳምንታዊ ትኩረት በዝርዝር ታይተዋል።
ምንም እንኳን የተኩስ አቁም ቢታወጅም ከሽሬ ከተማ በስተሰሜን በሚገኘው አዲ ዲአሮ ከተማ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች እና የህወሃት ሃይሎች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ዘገባዎች የሚያሳዩ ሲሆን በዚህ ምክንያት ውጊያው ተራዝሟል። የህወሃት ሃይሎች እስካሁን ከአጎራባች የአማራ ክልል በመጡ የፖሊስ እና ሚሊሻ ሃይሎች ወደሚጠበቀው ምዕራብ ትግራይ አልገቡም።
ወታደሮች ከህወሀት መምጣት ጋር ተያይዞ በፍጥነት እንደመውጣታቸው በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች ላይ የደረሰውን ትክክለኛ የጉዳት መጠን ለመገመት አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም ከተኩስ አቁሙ በፊት ሁለቱም ሀይሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቻቸው እንደሞቱ የሚገመት ሲሆን አለም አቀፍ ጋዜጠኞች እስከ 7,000 የሚደርሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት መማረካቸውን ዘግበዋል (ኤንዋይቲ፣ ሰኔ 25, 2013)። የመንግስት ምንጮች የተወሰኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “ሰላማዊ ሰዎችን ከመግደል ይልቅ እጃቸውን እንደሰጡ” ሆኖም ግን በህወሃት ተይዘዋል የተባሉት አባላት ቁጥር የተጋነነ ነው ብለዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 26, 2013)።
የሕወሃት ኃይሎች የተከዜ ወንዝን ተሻግረው ከምዕራብ ትግራይ ዞን አካባቢዎች የአማራ ክልላዊ ኃይሎችን ለማፈናቀል መሞከራቸው ስለማይቀር በሚቀጥሉት ሣምንታት ውጊያው ዳግም ሊነሳ ይችላል። ሰኔ መጨረሻ ላይ የተከዜ ወንዝ ድልድይ ተጎድቶ ለማለፍ የማይቻል በመሆኑ ለሰብአዊ እርዳታ ጉዞዎች አስቸጋሪ አድርጏታል። የፌዴራል መንግስቱ እና ህወሃት ድልድዩ ላይ ጉዳት ለመድረሱ አንዱ ሌላውን ይከሳሉ (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማብራሪያ፣ ሰኔ 25, 2013; ሮይተርስ፣ ሰኔ 25, 2013)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን ሆሮ ጉዱሩ በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ሆሮ ቀበሌ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች ከገበያ ሲመለሱ የነበሩ ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል። የሟቾቹን አስከሬን ለመውሰድ የመጡ ስድስት ተጨማሪ የወረዳ ታጣቂዎች በኦነግ-ሸኔ ተገድለዋል (ኢሳት፣ ሰኔ 21, 2013)። የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ባሳለፍነው ዓመት በምዕራብ ኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች እየጠነከሩ መጥተዋል (የኢፒኦን ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ የግጭት ዘገባ ገፅ ይመልከቱ)።
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግስት 50,553 ተፈናቃዮችን ወደ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች በማዘዋወር በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የራንቺ የተፈናቃዮች ካምፕ ዘግቷል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 23, 2013)። በካምፑ ውስጥ የሚኖሩ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች በመተከል ከሚገኙ መኖሪያዎቻቸው በ2012 ሁለተኛ መንፈቅ-አመት እና በ2013 የደረሱ ጥቃቶችን ተከትሎ የተፈናቀሉ ነበሩ። አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች አማራዎች ሲሆኑ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ውስጥ አናሳ ብሔር ናቸው፡፡ መንግስት እነዚህን ተፈናቃዮች ከሁለት ሳምንት በፊት በመተከል ዞን ወደሚገኙት የዳንጉር፣ ድባቴ፣ ማንዱራ፣ ቡለን፣ እና ወንበራ ወረዳዎች ማዘዋወር ጀምሯል (ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 12, 2013 እስከ ሰኔ 18, 2013 ይመልከቱ)። የመልሶ ማስፈሩ ሂደት በሎጂስቲክስና ፀጥታ ጉዳዮች ምክንያት የተስተጓጎለ ሲሆን ወደቦታዎቹ የተመለሱ ተፈናቃዮች የምግብ እጥረት መኖሩን እና ያልተፈቱ የፀጥታ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልፀዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 18, 2013)።
የመንግስት ሀላፊዎች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ምስራቃዊ አካባቢዎች ያልተፈቱ ችግሮችን ከአከባቢው ህዝብ ጋር በመወያየት ለመፍታት እየሞከሩ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት በማንዱራ ወረዳ በፖህቶማንጃሪ ቀበሌ ባህላዊ የእርቅ ስብሰባ ተካሂዷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 23, 2013)። ግንቦት ወር አጋማሽ አካባቢ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መንግስት ተወካዮች እና በክልሉ ዳግም የውህደት ስልጠና በሚወስዱ የታጠቁ ቡድን አባላት መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል (ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሚያዚያ 30, 2013 እስከ ግንቦት 13, 2013 ይመልከቱ)። ከ2010 ጀምሮ በመተከል የሚደርሱ አብዛኛዎቹ ሞቶች ባልታወቁ የብሔር ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ አማራዎች ላይ ከሚፈፀሙ ጥቃቶች ጋር የተያያዙ ናቸው (የኢፒኦን መተከል ግጭት ገፅን ይመልከቱ)።
ሳምንታዊ ትኩረት: የፌደራል መንግስት የአንድ ወገን ተኩስ አቁም ውሳኔ እና በትግራይ ክልል ያለው ግጭት
የፌዴራል መንግስት ሰኔ 21, 2013 በትግራይ ክልል ላይ ያሳለፈውን የተኩስ ማቆም ውሳኔ በሀገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያልተጠበቀ ሲሆን ካለፉት ወራት የተለየ የፖሊሲ አካሄድ ያሳየ ነው (ኤፒ፣ ሰኔ 21, 2013፤ ሮይተርስ፣ መጋቢት 16, 2013)። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች ትግራይ ክልልን ለቀው ሲወጡ የህወሃት ታጣቂዎች ደግሞ እየጨፈሩ ወደ ክልሉ ዋና ከተማ ገብተዋል (ቢቢሲ፣ ሰኔ 22, 2013)።
በፌደራል መንግስቱ እና ህወሃት መካከል የተከሰተው ከባድ ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 25, 2013 ላይ ነበር። የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ሩቅ አካባቢ የሚገኙ የክልሉ ተራራማ መንደሮች ውስጥ በመግባት እንደገና መደራጀታቸውን ተከትሎ ለፌደራል ወታደሮች አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል (የኢፒኦን የትግራይ ግጭት ገፅ ይመልከቱ)። በመሬት ላይ የፌዴራል ኃይሎች ስለአካባቢው የተሻለ እውቀት ካላቸው የክልል ኃይሎችና እና የአካባቢ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት የኤርትራ ወታደሮችን መግባት እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ጥቃት ምክንያት መአቀብን የጨመረ የዲፕሎማሲ ጫና ውስጥ ወደቁ (ኤንዋይቲ፣ ግንቦት 16, 2013; ኢቢሲ፣ ሰኔ 26, 2013)። የፌደራል መንግስቱ እየመጣ ባለው የሰብአዊ እና ወታደራዊ አደጋ ምክንያት ለቆ ሊወጣ ወስኗል።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ እንዳሳወቀው ወታደራዊ ንብረቶችን በማስመለስ እና የህወሓትን ከፍተኛ አመራሮችን በመያዝ ወይም በመግደል ወደክልሉ የገባበትን ዓላማዎቹን በማሳካቱ መውጣቱን ገልጿል። በተጨማሪም እርምጃውን የትግራይ አርሶ አደሮችን ሰላማዊ የመዝራት ወቅት እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን አሳውቋል (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማብራሪያ፣ ሰኔ 23, 2013)። የመንግሥት ሚዲያዎችም የዝናብ ወቅት መሆኑን ተከትሎ የሀገሪቱን ሀይድሮ ኤሌክትሪክ የሚያመነጨው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሞላት ስለሚጀምር ሀገሪቷ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር የዲፕሎማሲ ፍጥጫ ላይ በሆነችበት በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚገኙ ወታደሮች ወደምዕራብ ወሰኖች እንደሚቀየሩ አስታውቀዋል (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰኔ 23, 2013፤ ፍራንስ 24፣ ሰኔ 29, 2013)።
ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው የትግራይ ቀውስ ገና አላቆመም። ላለፉት ስምንት ወራት ህወሃት አመፅ እየፈጠረ በነበረበት ወቅት የትግራይን ክልል በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደሮች ማስተዳደር የማይቻል ሆኗል፡፡ በግጭቱ የመጀመሪያዎቹ ሳምንቶች ውስጥ ክልሉን በወታደራዊ ኃይል ማጣቱን ተከትሎ ህወሃት የፌደራል መንግስቱ የሾማቸውን ሃላፊዎች በመግደል እና የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን የሚደረጉ ጥረቶችን በማደናቀፍ በኋላ በፌዴራል የተሾሙትን ጊዜያዊ ባለሥልጣናትን በመግደል እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት በመፍጠር ክልሉን ማስተዳደር እንዳይቻል አድርጏል (የኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ እውነት ማጣሪያ፣ ግንቦት 18, 2013፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ሰኔ 28, 2013)። ሰርጎ ገብነት እየጨመረ በሄደበት ወቅት በክልሉ ቁጥጥር ማድረግ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ መንግስት በስራቸው ያሉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ማጥቃታቸው በተነገረው የኤርትራ ኃይሎች ተደግፏል (ኤፒ፣ የካቲት 11, 2013)።
በግጭቱ ወቅት የትግራይ ህዝብ በጎረቤት ሀገር ኤርትራ ወታደሮች ጭፍጨፋ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ የግንኙነት መቋረጥ፣ የውሃ መቋረጥ፣ እና ወሳኝ የእርሻ አቅርቦቶችን ዘረፋ በመሳሰሉ ህገወጥነቶች ተጎድቷል። ጋዜጠኞች ያገኟቸው ጠንካራ ማስረጃዎች በክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች ረሃብ መጀመሩን ያሳያሉ (ኤፒ፣ ሰኔ 23, 2013)።
በፌዴራል ባለሥልጣናት እና ህወሃት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ክልሉ ወደ መደበኛ ሁኔታ የሚመለስበትን እድል ያወሳስበዋል። ሚያዚያ 28, 2013 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃት ‘አሸባሪ’ ተብሎ እንዲሰየም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል (የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ሚያዚያ 28, 2013)። የህወሃት ኃይሎች ባለፈው ሳምንት መቀሌ ከተማን ሲቆጣጠሩ በፌደራል መንግስቱ ከሚደገፈው የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸውን 38 ግለሰቦችን ገድለዋል (የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሰኔ 26, 2013)። ይህ በርካታ የጊዜያዊ መንግስቱ ባለሥልጣናት በግጭቱ ወቅት በህወሃት ከመገደላቸው የቀጠለ ነው (የኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ እውነት ማጣሪያ፣ ግንቦት 18, 2013፤ ኢቢሲ፣ ሰኔ 20, 2013)።
በክልሉ ውስጥ ያለው የአስተዳደር ስራ ቆሟል፡፡ ከሰኔ 22, 2013 ጀምሮ የስልክ፣ ባንክ፣ እና ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን የተከተለው የገንዘብ እጥረት ቀድሞውኑ በጭንቅ ባለ ማህበረሰብ ላይ የደረሰ በመሆኑ ድንጋጤ ፈጥሯል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 25, 2013)። የፌዴራል መንግሥቱ ከዚህ በኋላ በከተማው ውስጥ ላሉ መሠረተ ልማት ሥራዎች አገልግሎት ኃላፊነት እንደማይወስድ ገልጿል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 26, 2013)። የነዳጅ አቅርቦት መስመሮች በስተሰሜን በኤርትራ፣ በምዕራብ በአማራ ክልል ኃይሎች፣ እና በምሥራቅ እና በደቡብ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተዘጉ በመሆናቸው ሕወሃት እነዚህን የመሰሉ ተግባራትን በራሱ የመመለስ አቅሙ አነስተኛ ነው።
በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የአስተዳደር ቀውስ ውስጥ ገብቷል፡፡ ለክልሉ ተገቢውን የአመራር ስራ የማቅረብ አቅም ያለው ክፍል (የፌዴራል መንግስት) በህወሃት ሰርጎ ገብነት ምክንያት ይህንን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። በአሁኑ ወቅት አብዛኛዉን የክልሉን ክፍሎች የሚቆጣጠረው ህወሃት ደግሞ ህዝቡ በጣም የሚያስፈልገውን ቁሶች እና አገልግሎቶች ለማቅረብ ያለው ችሎታ ትንሽ ነው። በተጨማሪም ሕወሓት ለጋራ ተኩስ አቁም ስምምነት ያቀረባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች ውስጥ የግዛት ነፃነትን ከፌዴራል መንግስት ገንዘብ ጋር እንደመጠየቁ፣ ከማዕከላዊው መንግሥት ግቦች ጋር በቀጥታ የሚቃረን ነው (አልጀዚራ፣ሰኔ 27, 2013)።
ውጊያው የሚያበቃ አይመስልም፣ የአንድ ወገኑ የተኩስ አቁም ውሳኔም ቀጣይነት ያለው ሰላም የማስፈን እድሉ ጠባብ ነው። ህወሃት የተኩስ አቁም ውሳኔውን “ቀልድ” ብሎ በመጥራት የኤርትራን ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን፣ እና የአማራ ክልል ሀይሎችን ተከትሎ ለማጥቃት ቃል ገብቷል (ሮይተርስ፣ ሰኔ 23, 2013)። 7,000 የሚሆኑ የማረኳቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ናቸው ያላቸውን ግለሰቦች በመቀሌ በህዝብ መሃል ማሳየቱ ህወሃት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንዳልተቀበለ ያሳያል።
እንደተጠቀሰው የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔው ከተላለፈ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ትግራይ ክልልን ለቆ ከወጣ ከአንድ ቀን በኋላ ሰኔ 22, 2013 ላይ በሰሜን ምዕራብ አዲ ዳእሮ በኢትዮጵይ እና ኤርትራ ወታደሮች እና በህወሃት ታጣቂዎች መካከል አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ተዘግቧል (ከስር ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። እንዲሁም ሰኔ 24, 2013 ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ዋና መግቢያዎች የነበሩት ሁለት የተከዜ ወንዝ ድልድዮች የወደሙ ሲሆን የፌዴራል መንግስት እና ህወሃት እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው (የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማብራሪያ፣ ሰኔ 25, 2013፤ ሮይተርስ፣ ሰኔ 25, 2013)። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአሁኑ ወቅት የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማመቻቸት በተከዜ ወንዝ ላይ ጊዜያዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለመገንባት እና በድልድዩ ዙሪያ የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ እየሞከሩ ነው (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 25, 2013)። ሰኔ 26, 2013 ላይ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ራማ በተባለ አካባቢ ከኤርትራ ወታደሮች ጋር ውጊያ ያካሄዱት የህወሃት ሀይሎች መሸነፋቸው ተዘግቧል (ኤርትሪያን ፕሬስ፣ ሰኔ 26, 2013)።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
በኢትዮጵያ የምርጫ ደንብ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጠት ካበቃ በኋላ ባሉት 10 ቀናት የምርጫውን ይፋዊ ውጤት ማሳወቅ ነበረበት (የኢትዮጵያ ምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብ አዋጅ ቁጥር 1162/2011, አንቀጽ 62)። የምርጫ ቦርድ ከ942 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም እና ለክልል ምክር ቤቶች ከተደረጉ ውድድሮች ውስጥ የ618 የምርጫ ውጤቶች ወደ ምርጫ ቦርድ ዋና ጽሕፈት ቤት መላካቸውን አስታውቋል። ሆኖም ግን የተወሰኑ በተሳሳተ መንገድ የቀረቡ አለመግባባቶች ምርጫ ቦርድ የድምፅ አሰጣጡን ውጤት በይፋ እንዳያወጣ እያደረጉት ነው (የምርጫ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰኔ 22, 2013)። ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች 160 የምርጫ ክልሎችን የሚመለከቱ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች አቅርበዋል (የምርጫ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰኔ 22, 2013)፡፡ ቅሬታ ካቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚደረገው ምክክሮች አሁንም እየተካሄዱ ሲሆን ፓርቲዎች የክርክር ጥያቄዎቻቸውን በትክክለኛው መንገድ እንዲያቀርቡ ለመርዳት የሕግ ባለሙያዎች ተቀጥረዋል።
በተጨማሪም አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ እንደገና እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል የሚገኙ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች – የአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ፣ የአፋር ህዝብ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ እና የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ በሲዳማ ክልል የሚገኘው የሲዳማ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የነበሩ ስህተቶችን በመጥቀስ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል (የአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ ሰኔ 22, 2013፤ ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 22, 2013)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የኦሮሚያ ክልል ብሔራዊ የሽግግር መንግሥት ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል (ኦነግ፣ ሰኔ 24, 2013፤ አዲስ ስታንዳርድ፣ ሰኔ 19, 2013)፡፡ ሁለቱም ወገኖች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ማንኛውንም አካባቢ ስለማይቆጣጠሩ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለም፡፡ ሁለቱም ፓርቲዎች በመንግስት በኩል ጫና ተፍጥሮብናል በሚል ምክንያት ከምርጫው ራሳቸውን አግልለው ነበር፡፡ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ፣ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም፣ እና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል (የኦፌኮ መግለጫ፣ ሰኔ 16, 2013)። በአራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ ፓርቲ ክንፍ በቅርቡ የተቋቋመውን የኦሮሚያን ብሄራዊ የሽግግር መንግስት አውግዞ የስልጣን ሽግግር በምርጫ ብቻ መከናወን እንዳለበት ገልጿል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 26, 2013)።
ድህረ-ምርጫ ወቅትን በተመለከተ የአክሌድ ኢፒኦ ቡድን የሰራውን ዝርዝር ዘገባ ለማንበብ ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 12, 2013 እስከ ሰኔ 18, 2013 እና ልዩ ዘገባችንን ይመልከቱ።