በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ የካቲት 18, 2014) 1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,631
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 15,022
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 6,947
በቁጥር (ከየካቲት 12, 2014 እስከ የካቲት 18, 2014) 2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 17
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 37
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 22
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ውጊያዎች ቀጥለዋል። በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) እና በአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች መካከል በቂልባቲ ረሱ-ዞን 2 በርሃሌ፣ ኤረብቲ፣ ኮነባ፣ እና አባላ ወረዳ ውጊያ ተመዝግቧል። በተጨማሪም የትህነግ/ህወሓት ሃይሎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች ጋር በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ተዋግተዋል። በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት ስለተከሰቱ ጉዳቶች ምንም መረጃ የለም።
የካቲት 18 ላይ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ አዘዞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ በፖሊስ ሲፈተሽ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊሶች እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ህይወት አልፏል። ሌሎች ሰባት የፖሊስ አባላት እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ደግሞ ቆስለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 19, 2014)።
በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመባል የሚታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ከመንግስት ሃይሎች ጋር ውጊያውን ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት አክሌድ በኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መካከል ሰባት የውጊያ ኩነቶችን መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የካቲት 12 ላይ ኦነግ-ሸኔ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የጫነ መኪና ላይ የደፈጣ ጥቃት አድርሶ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወታደሮችን ገድሏል። በነጋታው ሁለቱ ቡድኖች በምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ በገለዴ ቀበሌ ተዋግተዋል። የካቲት 14 ላይ የኦነግ-ሸኔ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በጉጂ ዞን አዶላ ወረዳ ሃዳማ ውስጥ ውጊያ አድርጓል። በተጨማሪም ሁለቱ ቡድኖች በሰሜን ሸዋ ዞን ዋረ ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሳ ቀበሌ እና ኩዩ ወረዳ ቢሪቲ አካባቢ፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳ በርጋ ወረዳ ቀርቀርሳ፣ እና በምስራቅ ወለጋ ዞን በለቃ ዱለቻ ወረዳ ባንዲራ ቀበሌ እና ቦኔያ ቦሼ ወረዳ ተዋግተዋል። ኦነግ-ሸኔ ባንዲራ ቀበሌን መያዙን ተናግሯል (ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ የካቲት 19, 2014)።
በኦሮሚያ ክልል በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ወለጋ ዞን የአማራ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ቤቶች አቃጥለው በጊዳ አያና ወረዳ በነጌሶ ቀበሌ አምስት ሰዎችን እና ሃሮ አያና ቀበሌ አራት ሰዎችን እንዲሁም በኪረሙ ወረዳ ዶሮ ቀበሌ ሁለት ሰዎችን ገድለዋል። የካቲት 12 ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን በማጥቃት የጠረጠሯቸውን 11 ሰዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ጋላን ወረዳ ቱሉ አሊዮ ቀበሌ ተኩሰው ገድለዋል።
ባለፈው ሳምንት የጋምቤላ ነጻነት ግንባር መሪ “በሰላማዊ መንገድ የመታገል አላማ” እንዳላቸው ገልጸው ለመንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የካቲት 17, 2014)። መሪው መንግስት በክልሉ ያሉ ታጣቂ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለዋል።
ሳምንታዊ ትኩረት፡ የጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች – የግጭት ወቅታዊ ሁኔታዎች መግለጫ
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት በርካታ የዜና አውታሮች ወቅታዊ መረጃዎችን ያቀረቡ ሲሆን በርካታ ወረዳዎች ከኦነግ-ሸኔ በሆኑየጸረ-መንግስት ሃይሎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አረጋግጠዋል። ልክ እንደሌሎች የኢትዮጵያ ግጭቶች ሁሉ በኦሮሚያ ደቡባዊ ጫፍ ባሉ ዞኖች ውስጥ ዘርፈ ብዙ ሲሆኑ የአካባቢ እና ብሔራዊ የፖለቲካ ሁኔታን ያንፀባርቃል። በአካባቢው ያለው ድርቅን የመሳሰሉ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ፖለቲካዊ ይዘት ካላቸው የግጭቱ መንስኤዎች መካከል ባይሆኑም ህዝቡ ከታጣቂ ሃይሎች ጋር እንዲገናኝ በማስገደድ ለግጭት ምቹ ሁኔታዎችን ጨምረዋል።
የኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ታሪክ ከታዩት የከፋ የድርቅ ወቅቶች አንዱን እያስተናገዱ ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወቅታዊ ዝናብ አለመጣሉ ያለውን ግጦሽ እየጨረሰ ሲሆን ይህም አርብቶ አደሩ ህዝብ ውሃ ፍለጋ ብዙ ርቀት እንዲጓዝ አስገድዶታል (ዩኔሴፍ፣ ታህሳስ 27, 2014)። በሀገሪቱ ያሉ የከተማ አካባቢዎችም በችግር ላይ ያሉ አርሶ አደሮች ለስራ ፍለጋ ወደ ከተማ በመግባታቸው ተጣበዋል። የመንግስት እና የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ዕርዳታ ለመስጠት ቢሰማሩም ግጭቶች አንዳንድ በጣም የተጎዱ ህዝቦች ጋር ያለውን ተደራሽነት ወስኖታል።
ድርቁ ባለበት ሁኔታም ከኦነግ-ሸኔ በመጡ ታጣቂዎች የሚመራ ሽምቅ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ኦነግ-ሸኔ በጣም ጠንካራ የሆነው በኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ቢሆንም ቡድኑ በቦረና፣ ጉጂ፣ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖችም ጠንካራ እንቅስቃሴ አለው። የኦነግ-ሸኔ ደቡባዊ ግንባር ምክትል ኮማንደር ገመቺስ አቦዬ በኦነግ-ሸኔ ውስጥ ሁለተኛ ከፍተኛ አመራር ሲሆን ባለፉት ሶስት እና አራት ወራት የቡድኑን ግዛት በከፍተኛ ሁኔታ አስፍቷል።
የኦነግ-ሸኔ የግዛት ቁጥጥር ባለፈው ሳምንት በሌሎች የዜና አውታሮች በከፊል ተረጋግጧል። በርካታ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ኦነግ-ሸኔ በጉጂ ዞን ከሚገኙ 18 ወረዳዎች አራቱን3አራቱ ወረዳዎች ዋደራ፣ ሳባ ቡሮ፣ ጉሚ ኢዳሎ፣ እና ጉራ ዶላ ናቸው። ሁለት ተጨማሪ ወረዳዎች ሊበን (ነገሌ ከተማ ዙሪያ) እና አዶላ ከፍተኛ ፉክክር እየተደረገባቸው ነው። እንዲሁም በምዕራብ ጉጂ ዞን የሚገኙ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል (ሪፖርተር፣ የካቲት 16, 2014፤ ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 24, 2014)። በሁለቱም ዞኖች የአካባቢ አስተዳደሮች የፌደራል ወታደራዊ ድጋፍ አለመኖሩ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸው የአካባቢው የቀበሌ ታጣቂዎች ቡድኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር እና ከአርብቶ አደር እንቅስቃሴ እና ተያያዥነት ባላቸው ውሃና ግጦሽን መሰረት ያደረጉ ማህበረሰባዊ ግጭቶች መጨናነቃቸውን ገልጸዋል። በኦነግ-ሸኔ ቁጥጥር ስር ባሉ (ወይም አሉ በሚል በሚያከራክሩ) አካባቢዎች በድርቅ የተጎዱ ህዝቦች እየተቸገሩ ነው። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሚያዚያ 2013 ባወጣው ዘገባ አካባቢውን ለሰብአዊ እርዳታ አድራሾች “ለመድረስ አስቸጋሪ” የሆነ ሲል ይገልጸዋል (ተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ሚያዚያ 22, 2014)።
ልክ እንደሌሎች የኢትዮጵያ የብሔር ንቅናቄዎች ሁሉ የኦሮሞ የብሔርተኝነት እንቅስቃሴም (እና የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴዎች) ከቋንቋና መሬት ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው። በእነዚህ በአከራካሪ ግዛቶች ምክንያት ተደጋጋሚ ግጭት በሚነሳባቸው አካባቢዎች ኦነግ-ሸኔ እራሱን የግዛት ወረራዎች ዋና ተከላካይ አድርጎ ለማቅረብ እድል አግኝቷል። ይህ የኦነግ-ሸኔ ሃይሎች በመሬትና አስተዳደር ወሰን ላይ በሚነሱ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በሚነሱባቸው በተለይ የጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ የሚፈጠር ነው። ይህ አካሄድ ባለው ድርቅና የአርብቶ አደር ሕዝብ እንቅስቃሴ ምክንያት ከቅርብ ወራት ወዲህ እየተባባሰ መጥቷል። በምእራብ ጉጂ ዞን ታሪካዊ ግጭቶች ውስጥ ኦነግ-ሸኔ ስላለው ሚና የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦን የምዕራብ ጉጂ ግጭት ገፅ ይመልከቱ።
ምንም እንኳን ኦነግ-ሸኔ በደቡብ ኦሮሚያ በድርቅ በተጠቁ ማህበረሰቦች ውስጥ ዘልቆ ቢገባም አጠቃላይ የድርቁ አስከፊነት ቡድኑ እርዳታ ለማድረስ ያለው ነገር ባለመኖሩ ለዘለቄታው ቡድኑን ሊጎዳው ይችላል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ሳምንታት ምግብ፣ ውሃ፣ እና የእንስሳት መኖ ለማድረስ ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ይህም በኦሮሚያ ክልል ህዝብ በመንግስት ላይ ያለው አስተያየት ላይ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በቅርቡ በአካባቢው ጉብኝት አድርገዋል (ዋልታ፣ ጥር 26, 2014)። አብይ በቅርቡ እነዚህ አካባቢዎች በኦነግ-ሸኔ ላይ የሚካሄደው ውጊያ ቡድኑ ባለው ህዝባዊ ድጋፍ ምክንያት ተግዳሮት እንዳጋጠመው አምነዋል (ኢቢሲ፣ የካቲት 15, 2014)።
ድርቁ እየተባባሰ በሄደ ቁጥር ከግጦሽ እና ከውሃ ሃብቶች እጥረት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው የእርስ በርስ ግጭት እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። መንግስት እና የኦነግ-ሸኔ አመራር ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት የሚመርጡት መንገድ በህዝቡ አስተያየት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር እና በአካባቢው እየተካሄደ ያለው ሽምቅ ውጊያ እንዲሳካ ወይም እንዲከሽፍ ያደርጋል።