ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥቅምት 12-18, 2015
በሰሜን ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ዘገባዎች ቢያመላክቱም በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሂደዋል።
በሰሜን ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ዘገባዎች ቢያመላክቱም በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሂደዋል።
Pro-government demonstrations were held in numerous cities throughout Ethiopia amidst heavy fighting in the north and reports of civilian casualties.
የመንግስት ኃይሎች በትግራይ ክልል ሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረምን ጨምሮ ቁልፍ ከተሞችን መልሰው ተቆጣጠሩ።
Government forces regained control of key towns in Tigray region, including Shire, Alamata, and Korem.
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙትን ሁሉንም ኤርፖርቶችና ሌሎች የፌዴራል ተቋማትን መልሶ ለመቆጣጠር ያለውን አላማ ገልጿል።
The Ethiopian government stated its goal to regain control of all airports and other federal facilities in Tigray region.
የአፍሪካ ህብረት ትህነግ/ህወሓትን እና የፌዴራል መንግስትን በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ድርድር ላይ ጋብዞ ሁለቱም ወገኖች ጥሪውን ተቀብለዋል።
The AU invited the TPLF and the federal government to AU-led peace negotiations and both parties accepted the invitation.